125 አዳዲስ የገጠር ከተሞችና መንደሮች የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ሆኑ
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ኤሌክትሪክ ባልዳረሰባቸው የሃገሪቱ ከተሞችና መንደሮች ፍትሃዊ የኤሌክትሪክ ተደራሽነትን ዕውን ለማድረግ ዘርፈ ብዙ ሥራዎች እያከናወነ ይገኛል፡፡
በዚህም ተቋሙ በ2014 በጀት ዓመት ባለፉት ዘጠኝ ወራት ውስጥ 125 አዳዲስ የገጠር ከተሞችና መንደሮችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ማድረግ ችሏል፡፡
በዘጠኝ ወር በሪጅኖች ከ6 ቢሊየን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው የግብዓት ግዢ ውል ስምምነቶች መፈፀማቸውን ተገለፀ
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ያልተማከለ አደረጃጀትን ተግባራዊ ባደረገው መሰረት ባለፉት ዘጠኝ ወራት የሪጅን ፅህፈት ቤቶች ከሃገር ውስጥ የዲስትሪቢዩሽን ዕቃዎች አምራች ድርጅቶች ጋር በግብዓት አቅርቦት ዕቅድ መሰረት ግዢ ሲያከናወኑ መቆየታቸውን በተቋሙ የግዢ፣ ሎጅስቲክስ፣ ንብረትና ፋሲሊቲ ዳይሬክተር አቶ ኢሳያስ ደንድር ገልፀዋል፡፡
በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ግብዓት የግዢ ስርዓት ውስጥ በዋነኝነት ሀገር በቀል አምራች ድርጅቶችን አሳታፊ ለማድረግ አዲስ የግዢ መመሪያ በተቋሙ ስራ አመራር ቦርድ ፀድቆ ተግባራዊ መደረጉንም ዳይሬክተሩ አስታውቀዋል፡፡
የመሠረተ ልማት ስርቆት በፈፀሙ ተከሣሾች ላይ የቅጣት ውሣኔ ተላለፈ
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በ2014 በጀት ዓመት ባለፉት ዘጠኝ ወራት የተፈፀሙ እና ከባለፈው በጀት ዓመት የተዛወሩ ተቋሙን ከ84 ሚሊየን ብር በላይ ያሳጡ 3 መቶ 57 የተለያዩ የወንጀል ክሶች መስርቷል፡፡
ከእነዚህ ውስጥም በኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት ላይ ስርቆት በፈፀሙና ጉዳት ባደረሱ 20 ግለሰቦች ላይ የቅጣት ውሳኔ መተላለፉን በተቋሙ የህግ አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ አበበ ተስፋ አስታውቀዋል፡፡አቶ አበበ አክለውም እነዚህ 20 ተከሣሾች ጥፋተኝነታቸው ተረጋግጦ ከ6 ወር እስከ 12 ዓመት በሚደርስ እስራት እንዲቀጡ መወሰኑና ቀሪዎቹ ክሶች በሂደት ላይ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡
ዓለም አቀፍ የስራ ላይ ደህንነትና ጤና ቀን በድምቀት ተከበረ
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ19ኛ፤ በአገራችን ለ18ኛ ጊዜ የተከበረውን የዓለም አቀፍ የስራ ላይ ደህንነት ቀን ዛሬ በአዲስ አበባ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አዘጋጅነት በድምቀት አክብሯል፡፡
በዓሉ የተከበረው ‹‹የሙያ ደህንነትና ጤንነት ባህል ለመገንባት በጋራ እንረባረብ›› በሚል መሪ ቃል ሲሆን፤ በተቋም ደረጃ ለሁለተኛ ጊዜ የተከበረ ነው፡፡
ተቋሙ በህግ ማስከበርና ህልውና ዘመቻው ላደረገው አስተዋጽኦ ዕውቅና ተሰጠው
የኢትዮጽያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በህግ ማስከበርና በህልውና ዘመቻው ካደረገው ሁሉን አቀፋ አስተዋጽኦ ባለፈ በወራሪ ቡድኑ የወደሙ እና የተዘረፋ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶችን በከፋተኛ ርብርብ ጠግኖ እና ገንብቶ ወደ አገልግሎቱ መመለሱ ይታወሳል።
የአማራ ክልል ‘‘በህግ ማስከበርና በህልውና ዘመቻው የተከፈለ መስዋዕትነት ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና አንድነት’’ በሚል መሪ ቃል በባህር ዳር ከተማ ባካሄደው የእውቅና እና የምስጋና መርሀ ግብር ላይ ነው የኢትዮጽያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት እውቅናው የተሰጠው።