የሀዘን መግለጫ
Hits: 108
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሥራ አመራር ቦርድ፣ ማኔጅመንት እና ሠራተኞች በ4ኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ዕረፍት የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን እየገለጹ፣ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች እና ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ መጽናናትን ይመኛሉ፡፡
ተቋሙ በሪስክ ማኔጅመንት ላይ ሲሰጠው የቆየውን ስልጠና አጠናቀቀ
Hits: 145
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የኮርፖሬት ፕላኒንግ ሪስክ ማኔጅመንት ሥራ ክፍል 50 ለሚሆኑ ሠራተኞች በሪስክ ማኔጅመንት ላይ ለአምስት ተከታታይ ቀናት ሲሰጠው የቆየውን ስልጠና በዛሬው ዕለት አጠናቋል፡፡
ተቋሙ የሚሰጠውን አገልግሎት ለማቀላጠፍና በአግባቡ ለመመራት የአምስት ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ ነድፎ እየሰራ ሲሆን፤ የተቀመጡ ግቦችን ለማሳካትም ዘርፈ-ብዙ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል፡፡ የታቀዱ ዕቅዶችን እንዳይሳኩ ተግዳሮት የሚሆኑ ስጋቶችን ነቅሶ በማውጣት መፍትሄ ማበጀትም በተጓዳኝ እየተሰራበት ነው፡፡
905 ነፃ የጥሪ ማዕከል በቀን በአማካኝ ከ9 ሺህ ደንበኞች በላይ እንደሚያስተናግድ ተገለፀ
Hits: 140
በ905 የደንበኖች ነፃ የጥሪ ማዕከል በቀን በአማካኝ 9 ሺህ 373 ደንበኞችን እንደሚያስተናግድ የደንበኞች አገልግሎት ጥሪ ማዕከል ስራ አስኪያጅ አቶ ደረጀ አስማማው ገለፀዋል፡፡
የጥሪ ማዕከሉ ቅሬታ ለማቅረብ፣ ጥቆማ ለመስጠት፣ ስለተቋሙ መረጃዎችን ለማግኘት እንደሚያስችል አስታውሰው፤ አሁን ላይ በአንድ ጊዜ 55 ጥሪዎች እንደሚነሱና 1 መቶ 20 ደንበኞች በመስመር ላይ እንደሚጠብቁ አስታውቀዋል፡፡
ለመላው ጥቁር ሕዝቦች ኩራት ለሆነው የዓድዋ ድል መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን!
Hits: 131
ለመላው ጥቁር ሕዝቦች ኩራት ለሆነው የዓድዋ ድል መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን!
የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዛሬ በይፉ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት ጀመረ
Hits: 111
የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዛሬ በይፉ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት ጀመረ:: መላው ኢትዮጵያውያን እንኳን ደስ አለን! የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የስራ አመራር ቦርድ ማኔጅመንትና ሠራተኞች በዚህ ታላቅ ስኬት የተሰማቸውን ከፍተኛ ደስታ ይገልጻሉ፡፡
በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ! እንኳን ደስ አለን!
