በባቡር የኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማቶች ላይ የሚፈፀሙ የስርቆት ወንጀሎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ መምጣቱ ተገለፀ
በአዲስ አበባ ከተማ ለቀላል ባቡር በተዘረጉ የኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማቶች ላይ የሚፈፀመው የስርቆት ወንጀል ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ መምጣቱን የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ሥራ አስኪያጅ አቶ ቢልቱማ ቂጣታ ገልፀዋል፡፡
አቶ ቢልቱማ አክለውም የሚፈፀመው የስርቆት ወንጀል የሃገርን ኢኮኖሚ ወደኋላ ከማስቀረቱም በተጨማሪ በከተማዋ ያለውን የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት እንዲስተጓጎል እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጥ ምክንያቶችና የተቋሙ የመፍትሄ እርምጃዎች
የኤሌክትሪክ ኃይል በዕቅድ ወይም ያለዕቅድ በብልሽት ምክንያት ሊቋረጥ ይችላል፡፡ በዕቅድ የሚቋረጥ ሲባል ለተወሰነ ጊዜ ለሥራ አስፈላጊ ሲሆን ደንበኛን አስቀድሞ በማሳወቅ የሚቋረጥ ነው፡፡
በአሁን ወቅት ኤሌክትሪክ ሳይጠፋ ኃይል ማገናኘት የሚቻልበት የቴክኖሎጂ አቅም ላይ ስላልተደረሰ፤ የተቋሙ የቴክኒክ ሠራተኞች ሥራን ደህንነቱ በተጠበቀ መልኩ ማከናወን እንዲችሉ በዕቅድ የኃይል አቅርቦት ሊቋረጥ ይችላል፡፡
የስድስቱ በከተሞች የዲስትሪቢዩሽን መስመሮች ማሻሻያና ማስፋፊያ ፕሮጀክት አፈፃፀም 66 በመቶ መድረሱ ተገለፀ
ጥራት ያለውና አስተማማኝ አገልግሎት ለመስጠት ተቋሙ ከሚሰራቸው ስራዎች አንዱ በዓለም ባንክ የገንዘብ ድጋፍ የሚሰራው የስድስቱ ከተሞች የዲስትሪቢዩሽን ኔትዎርክ መልሶ ግንባታና አቅም ማሳደግ ፕሮጀክት ነው፡፡
ይህ ፕሮጀክት ከተጀመረ ከታህሳስ 2012 ዓ.ም ጀምሮ የከተሞች ኤሌክትሪክ መስመር መልሶ ግንባታ እና ሌሎች ልዩ ልዩ የግዢ ኮንትራቶች አፈጻጸም የፀጥታ ችግር ያለባቸው ከተሞችን ሳይጨምር 66 በመቶ እንደደረሰና በያዝነው በጀት ዓመት አንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል ሲሉ የፕሮጀክቱ ኃላፊ አቶ ምንተስኖት ተስፋዬ ገልፀዋል፡፡
አገልግሎቱ በጦርነቱ ለተጎዱ አገልግሎት መስጫ ማዕከላት ማቋቋሚያ የሚሆን ድጋፍ አደረገ
የአዲስ አበባ ከተማ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በአማራ ክልል ኤሌከትሪክ አገልግሎት በሶስት ዲስትሪክቶች ስር የሚገኙ በጦርነቱ ለተጎዱ አገልግሎት መስጫ ማዕከላት ማቋቋሚያ የሚሆን 1 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር የሚገመቱ የቢሮ መገልገያዎች ቁሳቁሶችን የካቲት 28 ቀን 2014 ዓ.ም ድጋፍ ማድረጉን አስታውቋል።
የተሰጠው የቢሮ ቁሳቁስ በጦርነቱ ጉዳት የደረሰባቸውን በወልድያ፣ ደሴ እና ደ/ብርሃን ዲስትሪክቶች ስር የሚገኙ የደንበኞች አገልግሎት መስጫ ማእከላት ለማቋቋም የሚያገለግል ነው::
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ያለፉት ስድስት ወራት የስራ አፈፃፀም ተገመገመ
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የ2014 በጀት ዓመት የስድስት ወራት የስራ አፈጻጸም በገንዘብ ሚኒስቴርና በመንግስት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር በዛሬው ቀን ተገምግሟል፡፡
አፈፃፀሙ በተገመገመበት ወቅት የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ እንደገለጹት መንግስት ለኢነርጂ ሴክተር ከፍተኛ ትኩረት የሰጠ በመሆኑ በጥንቃቄ የሚከታተለውና የሚመራው ዘርፍ ነው ብለዋል፡፡በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያው ትኩረት በተሰጠው የኢነርጂ ዘርፍ ኢትዮጵያን የምስራቅ አፍሪካ የታዳሽ ሀይል ምንጭ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ሚኒስትሩ ገልፀዋል፡፡