ከሳፋሪኮም-ኢትዮጵያ ጋር የኮንክሪት ምሰሶ ኪራይ ስምምነት ተፈረመ
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎትና ሳፋሪኮም-ኢትዮጵያ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የኮንክሪት ምሰሶ ኪራይ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡
ስምምነቱን የፈረሙት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ሽፈራው ተሊላና የሳፋሪኮም-ኢትዮጵያ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሚስተር አንዋር ሶውሳ ናቸው፡፡
ከባህር ዳር - ዳንግላ በሚሄድ 66KV አስተላለፊ መስመር በተፈፀመ ስርቆት የኤሌክትሪክ ኃይል ተቋርጧል
ከባህር ዳር - ዳንግላ በሚሄድ 66KV የኤሌክትሪክ አስተላለፊ የብረት ታወር ላይ በተለምዶ ቆጥቆጥማ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በተፈፀመ ስርቆት ምሰሶዎች በመውደቃቸው ከዳንግላ እና ፓዌ ማከፋፈያ ጣቢያ/ሰብስቴሽን/ ኤሌክትሪክ የሚያገኙ ከተሞች ኃይል ተቋርጦባቸዋል፡፡
በዚህም ምክንያት ዳንግላ፣ ዱርቤቴ፣ መራዊ፣ ኮሶበር፣ ግምጃ ቤት፣ ቻግኒ እና በአካባያቸው ባሉ ከተሞች ላይ የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጡን የአማራ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት አሳውቋል፡፡
የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ስርቆት የፈፀሙ ተጠርጣሪዎች እጅ ከፍንጅ መያዛቸው ተገለፀ
በአዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ አከባቢዎች በተለይም በሌሊቱ ክፍለ ጊዜ በቡድን በመደራጀት የኤሌክትሪክ በመሰረተ-ልማት ስርቆት የፈፀሙ ግለሰቦች እጅ ከፍንጅ ተይዘው ምርመራው እየተደረገባቸው መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ከሚሽኑ አስታውቋል፡፡
የቀላል ባቡር የኃይል ማስተላለፊያ ኬብል በመቁረጥ ሲዘርፉ የነበሩ ግለሰቦች በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ልዩ ቦታው ንግድ ባንክ አካባቢ ተመሳሳይ ስርቆት ሲፈፅሙ በወንጀል መከላከል ስራ ላይ በነበሩ የፖሊስ አባላት እጅ ከፍንጅ እንደተያዙ የየካ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር ደመና ተስፋዬ ገልፀዋል፡፡
የኃይል ስርቆት ሲፈፅሙ የተገኙ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ
በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ ሽሮሜዳ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በጥቃቅንና አነስተኛ ማህበር በተደራጀ አንድ ማዕከል ውስጥ በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ የኤሌክትሪክ ኃይል ስርቆት ሲፈፅሙ የተገኙ 11 ተጠርጣሪዎች በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑ በአዲስ አበባ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የኢነርጂ ማኔጅመንት ሥራ አስኪያጅ አቶ አስናቀው ፀሐይ ተናግረዋል፡፡
ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት መጋቢት 2 ቀን 2014 ዓ.ም የአገልግሎቱ ኢነርጂ ማኔጅመንት ቢሮ የኢንስፔክሽን ባለሙያዎች በአካባቢው ከሚገኙ የፖሊስ አካላት ጋር በመተባባር ባደረጉት ድንገተኛ የፍተሻ ስራ ሲሆኑ፤ ግለሰቦቹ ከተፈቀደላቸው የኃይል መጠን ውጭ ሲጠቀሙ መገኘታቸው ሥራ አስኪያጁ ገልፀዋል፡፡
የቅድመ-ክፍያ ተጠቃሚ ደንበኞች ከተጨማሪ ወጪ እንዲድኑ በየወሩ ኃይል መግዛት አለባቸው
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከአራት ሚሊዮን በላይ የቅደመና የድህረ-ክፍያ ተጠቃሚ ደንበኞች አሉት፡፡ የቅደመ-ክፍያ ደንበኞች የሚባሉት ለአንድ ወር የሚሆን የኤሌክትሪክ ኃይል ገዝተው የሚጠቀሙ ሲሆን፤ የድህረ-ክፍያ ደንበኞች ደግሞ ለአንድ ወር ያህል የኤሌክትሪክ ኃይል ከተጠቀሙ በኃይል የፍጆታ ክፍያ የሚፈፅሙ ናቸው፡፡
የቅደመ ሆነ የድህረ-ክፍያ የመኖሪያ ቤት ደንበኞች በየወሩ የሚገዙት ኃይል ወይም የሚከፍሉት የፍጆታ ሂሳብ የተጠቀሙበትን የኤሌክትሪክ ኃይል እና የአገልግሎት (በተለምዶ የቆጣሪ) ክፍያ ድምር ነው፡፡