በህገ-ወጥ መንገድ በተዘረጉ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ
በሐረሪ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት በሐረርቁ.2 አገልሎት መስጫ ማዕከል ስር ሃማሬሳ አካባቢ ገንደ ኖሌ እንዲሁም ሜሽን አካባቢ አዲሱ ሰብእስቴሽን ጀርባ በህገ-ወጥ መንገድ የተዘረጉ የኤሌክትሪክ መስመሮችን የማፍረስ እና የተገጠሙ ቆጣሪዎችን የማንሳት እርምጃ ተወስዷል፡፡
ገ-ወጥ ስራ ላይም የዋሉ እቃዎች 5 ቆጣሪዎች እነዲሁም 8 የእንጨት ምሶሶ በቀን 16/9/2014 ዓ.ም ከሐረሪ ክልል ፖሊስ ኮምሽን ጋር በጋራ በመሆን እርምጃው መወሰዱን የሐረሪ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ነገረ ፈጅ አቶ ዳንኤል አባይነህ ገልፃዋል፡፡
በከንባታ ጠንባሮ ዞን በ33 ኪሎ ቮልት የኤሌክትሪክ መስመር ላይ ጉዳት ደረሰ
በደቡብ ክልል ከንባታ ጠንባሮ ዞን ቃጫ ቤራ ወረዳ ልዩ ስሙ ጨጫ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ ከሆሳዕና እስከ ዱራሜ በተዘረጋው 33 ኪሎ ቮልት የኤሌክትሪክ መስመር ላይ ጉዳት መድረሱን የደቡብ ክልል ኤሌከትሪክ አገልግሎት አስታውቋል፡፡
በዚህም በ27 ምሶሶዎች ላይ የተዘረጋ የኤሌክትሪክ መስመር ተዘርፎ ሙሉ ለሙሉ ከጥቅም ውጪ መሆኑ ተገልጿል።
ዲስትሪክቱ ጥራት ያለው አገልግሎት ለመስጠት በትኩረት እየሰራ መሆኑን ገለፀ
በአማራ ከልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት የደብረ ብርሃን ዲስትሪክት ጥራት ያለውና አስተማማኝ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ለመስጠት በትኩረት እየሰራ መሆኑን አስታውቋል፡፡
የዲስትሪክቱ ዳይሬክተር አቶ ሙሉጌታ ደሳለኝ እንደገለፁት፡- ዲስትሪክቱ የደንበኞችን ቅሬታዎች ደረጃ በደረጃ ለመፍታት፣ የኃይል መቆራረጥና መዋዥቅን ለመቀነስ፣ የመልሶ ግንባታ ስራዎችን ለማጠናከር እና ከባለፈው በጀት ዓመት የተሻለ ገቢ ለመሰብሰብ ትኩረት ሰጥቶ በመንቀሳቀስ ላይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በህገ-ወጥ መንገድ በተዘረጉ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ
በአዲስ አበባ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የምስራቅ አዲስ አበባ ዲስትሪክት ቁጥር 5 አገልግሎት መስጫ ማዕከል በከተማው በህገ-ወጥ መንገድ የተዘረጉ የኤሌክትሪክ መስመሮችን የማፍረስና የተገጠሙ ቆጣሪዎችን የማንሳት እርምጃ ወስዷል፡፡
እርምጃው የተወሰደው ልዩ ስሙ ወጂ መድሐኔአለም ሰፈር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ሲሆን፤ ግለሰቦቹ በህገ-ወጥ መንገድ የኤሌክትሪክ መስመሮች ዘርግተው የኤሌክትሪክ ቆጣሪ ሲጠቀሙ እንደነበር የአዲስ አበባ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የህግ ጉዳዮች ሥራ አስኪያጅ አቶ ታሪኩ ማዕረጉ ገልፀዋል፡፡
የሲዳማ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጽ/ቤት በይፋ ስራ ሊጀምር ነው
የሲዳማ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጽ/ቤት ከሚቀጥለው ሐምሌ /2014 ዓ.ም ጀምሮ ስራውን በይፋ ሊጀምር እንደሆነ ተገልጿል፡፡ ይህ የተገለፀው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የቦርድ ሰብሳቢ ዶክተር ኢንጅነር ጌታሁን መኩሪያ፣ የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት አቶ ደስታ ሌዳሞ፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሽፈራው ተሊላ፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከፍተኛ የማናጅመንት አባላት እና የደቡብ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ማናጅመንት አባላት በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ቢሮ ግንቦት 12/2014 ዓ.ም ባደረጉት የጋራ ስብሰባ ላይ ነው፡፡