የቡሳ ቀበሌ ነዋሪዎች የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ሆኑ
በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ አርሲ ዞን ወንዶ ገነት ወረዳ ቡሳ 02 ቀበሌ ነዋሪዎች የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡ የኦሮሚያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በአገር አቀፍ የኤሌክትሪክ አቅርቦት ፕሮግራም ጽ/ቤት በበጀት አመቱ የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግ ከያዛቸው የገጠር ከተሞችን ውስጥ አንዱ የሆነው የቡሳ 02 ቀበሌ የገጠር ከተማ ነዋሪዎች የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ለመሆን ችሏል፡፡
የከተማዋ ነዋሪዎች ለረጅም ዘመናት የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ለመሆን ሲጠይቁ የነበረ ሲሆን የአገር አቀፍ ኤሌክትሪክ አቅረቦት ፕሮግራም ጽ/ቤት የነዋሪዎቹን ቅሬታና ጥያቄ ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት በጀት በመመደብ ወደ ስራ የገባ መሆኑን በሻሸመኔ ዲስትሪክት የፕሮጀክት አስተባባሪ የሆኑት አቶ ሁሴን ቴሶ ተናግረዋል፡፡
የተገልጋዮች ቻርተር-ግልጽነትና ተጠያቂነት ለተሞላበት አገልግሎት
ሀገራችን መልካም አስተዳደርንና ልማትን በማረጋገጥ ህዝቦቿን ከድህነት ለማውጣት እና መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገራት ተርታ ለማሰለፍ የያዘቸውን ራዕይ ለማሳካት የኤሌክትሪክ አገልግሎት የማይተካ ሚና ይጫወታል፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎትም ለማህበራዊም ሆነ ምጣኔ ሃብታዊ ዕድገት ከፍተኛ ሚና ያለውን የኤሌክትሪክ አገልግሎት በፍትሃዊ መንገድ ለሁሉም ዜጋ እንዲደረስ ለማድረግ በርካታ ተቋማዊ ማሻሻያዎችን በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡
የስድስቱ ከተሞች የዲስትሪቢዩሽን መስመር መልሶ ግንባታና አቅም ማሳደግ ፕሮጀክትን በተያዘለት ጊዜ ለማጠናቀቅ እየተሰራ ነው

ብልሹ አሠራርን ለመከላከል የሚያስችሉ ስርዓቶች ተግባራዊ እየተደረጉ መሆኑ ተገለፀ
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በተለያዩ ደረጃ የሚስተዋሉ ብልሹ አሰራሮችን ለመከላከል የሚያስችሉ የአሠራር ስርዓቶችን እያከናወነ እንደሚገኝ የተቋሙ የስነ-ምግባርና ፀረ ሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ህብረወርቅ ይመኑ ገለፁ፡፡
ተቋሙ ከዚህ በፊት ሲሰጥ የነበረው የአገልግሎት አሰጣጥ ዘመናዊ ያልሆነ፣ ለብልሹ አሰራር የተጋለጠ እና ለቁጥጥር የማይመች እንደነበር የገለጹት አቶ ህብረወርቅ ይንንም ለመቅረፍ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ለሙስና ምንጭ የሆኑ አሰራሮችን መቀነስ ተችሏል ብለዋል፡፡
ከ17 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት የወልቂጤ የደንበኞች አገልግሎት መስጫ ማዕከል የቢሮ ህንፃ ግንባታ ተጠናቆ ተመረቀ
