የቆጣሪ ማንበቢያ መሳሪያው ከንባብ ጋር የተያያዙ ችግሮችን በመቅረፍ ረገድ ትልቅ ለውጥ ማምጣቱን ተገለፀ
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በስራ ላይ ያዋለው ዘመናዊ የቆጣሪ ማንበቢያ መሳሪያ ከቆጣሪ ንባብ ጋር በተያያዘ የሚስተዋሉ ችግሮችን በመቅረፍ ረገድ ትልቅ ለውጥ ማምጣቱን በተቋሙ የደንበኞች አገልግሎት ሃላፊ ወ/ሮ ፍሬህይወት ወርቁ ገልፀዋል፡፡
ንደ ወ/ሮ ፍሬህይወት ገለፃ በስራ ላይ የዋለው ዘመናዊ የቆጣሪ ማንበቢያ መሳሪያው (ኮመን ሜትር ሪዲንግ ኢንስትሩመንት) የቆጣሪ አንባቢ ባለሞያ በእያንዳንዱ ደንበኛ ቤት ሄዶ እንዲያነብ የሚያስገድድ በመሆኑ፤ ከወርሃዊ የፍጆታ ሂሳብ ጋር በተያያዘ የሚቀርቡትን ቅሬታዎች ከመቀነሱም በተጨማሪም ደንበኞች የፍጆታ ሂሳባቸውን በወቅቱ እንዲከፈሉ በማድረግ የተቋሙን ገቢ በተገቢው መንገድ ለመሰብሰብ የሚደረገውን ጥረት በከፍተኛ ሁኔታ እየደገፈ ይገኛል፡፡
የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሑመራ አካባቢን የኤሌክትሪክ ችግር በአጭር ጊዜ ለመፍታት እንዳልተቻለ ተገለፀ
የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሑመራ አካባቢን የኤሌክትሪክ ችግር በአጭር ጊዜ ለመፍታት አለመቻሉን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታውቋል፡፡
በሽብር ቡድኑ ምክንያት የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሑመራ ኃይል ከተቋረጠ ከአንድ ዓመት በላይ ሲሆን፤ የላሊበላ እና የዋግ ኽምራ ዞን በርካታ አካባቢዎችም ለወራት የኤሌክትሪክ ኃይል እያገኙ አይደለም፡፡
አጠቃላይ የግዥ ስርዓት ሂደትን የተመለከተ ስልጠና ተሰጠ
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከፍተኛ አመራሮች ጨምሮ ሌሎች በተቋሙ የግዥ ሥራዎች የሚያከናዉኑ አካላት የተሳተፉበት በአጠቃላይ የግዥ ስርዓት ላይ ያተኮረ ስልጠና ዛሬ ሚያዚያ 3 ቀን 2014 ዓ.ም ተሰጥቷል፡፡
ስልጠናው የተሰጠው ከአለም ባንክ በመጡ ከፍተኛ የግዥ ባለሙያ ሲሆን፤ የስልጠና ዋና ዓላማ በተቋሙ የግዥ ስርዓት ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ እና የግዥ ስርዓቱን ቀልጣፋና ውጤታማ ለማድረግ ነው፡፡
ነባሩን የኤሌክትሪክ ቆጣሪ በዘመናዊ ስማርት ቆጣሪዎች የመተካት ስራ ለከፍተኛ ኢንደስትሪ የኃይል ተጠቀሚ ደንበኞች መቀየር ተጀመረ
ለከፍተኛ ኢንደስትሪ የኃይል ተጠቀሚ ደንበኞች አድቫንስድ ቆጣሪዎችን ከመጋቢት 24 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ መግጠም መጀመሩን የአድቫንስድ ሜትሪንግ ኢንፍራስትራክቸር እና ስካዳ ፕሮጀክት ኃላፊ አቶ ጩመላ ሳሙኤል አስታውቀዋል፡፡
በሙከራ ደረጃ 100 ቆጣሪዎችን በአዲስ አበባ በሁሉም ዲስትሪክቶች ለመቀየር በታሰበው መሰረት እስካሁን 24 አድቫንስድ ቆጣሪዎችን ለማስገባት መቻሉን ኃላፊው ገልፀዋል፡፡
ተቋሙ በመንግስት ልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ተጎበኘ
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠሪ የሚሆንለት የመንግስት ልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር በተቋሙ የመጀመሪያውን የመስክ ጉብኝት ዛሬ መጋቢት 29 ቀን 2014 ዓ.ም አካሂዷል፡፡
መስክ ምልከታ ጉብኝቱን ያከናወኑት የመንግስት ልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ከፍተኛ የስራ አመራሮች ሲሆኑ፤ በጉብኝቱ ወቅትም የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ ሽፈራው ተሊላን ጨምሮ ሌሎች የተቋሙ ከፍተኛ የስራ አመራሮች ተሳትፈውበታል፡፡