የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በኮዬ ፈጬ ኮንዶሚኒየም ቆጣሪ በጋራ ይጠቀሙ ለነበሩ ከ30 ሺህ በላይ አባወራዎች የነጠላ ፌዝ ስማርት ቆጣሪ ገጠማ አከናወነ፣
የቆጣሪ ገጠማ ሥራው የተከናወነው የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት ዝርጋታ ሥራ በተጠናቀቀባቸው የኮዬ ፈጬ ፕሮጀክት 11እና 18  እንዲሁም የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት ዝርጋታ ሥራ ባልተጠናቀቀባቸው የፕሮጀክት 17፣12፣16፣ ነፋስ ስልክ፣ አቃቂ 1፣ አቃቂ 2 እና ሌሎች ሳይቶች  ነው፡፡
እነዚህን ነዋሪዎች የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግ 17.3 የዝቅተኛ መስመር፣ 8.4 ኪ.ሜ የመሬት ውስጥ ተቀባሪ መካከለኛ መስመር ዝርጋታ እንዲሁም 4.1 ኪ.ሜ የዝቅተኛ መስመር የአየር ላይ መስመር ዝርጋታ ተከናውኗል፡፡
በተጨማሪም 11 ባለ 630 ኬ.ቪ.ኤ ትራንስፎርመር፣ 21 ባለ 800 ኬ.ቪ.ኤ እና 21ባለ 1250 ኬ.ቪ.ኤ ትራንስፎርመሮች እንዲተከሉ ተደርጓል፡፡
የፕሮጀክት 12፣16፣17 ነፋስ ስልክ፣ አቃቂ 1፣ አቃቂ 2 እና ሌሎች ሳይት ነዋሪዎችን ሙሉ በሙሉ የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግ የኮምፓክት ትራንስፎርመርና የመሬት ውስጥ ተቀባሪ ኬብሎች እንዲቀርቡ ተደርጓል፡፡
ይህም ደንበኞች ወርኃዊ የኃይል ፍጆታ አከፋፈል ላይ እያጋጠማቸው ያለው ችግር እንዲቀረፍና እንደ ኃይል አጠቃቀማቸው ክፍያ እንዲፈፅሙ አስችሏል፡፡
ውድ ደንበኞቻችን
አገልግሎታችንን ቀልጣፋ፣ ተደራሽ እና የእርስዎን ፍላጎት ያማከለ ለማድረግ ዝግጁ ነን! ከአገልግሎታችን ጋር በተያያዘ ማንኛውም ችግር ወይም ቅሬታ ሲገጥምዎ በ9105 አጭር የጽሁፍ መልዕክት (SMS) ያሳውቁን።
💬 አስተያየትዎን ያካፍሉ
📝 ቅሬታዎን ያሳውቁ
⚡️ የኃይል መቋረጥን ይጠቁሙ
📌 ጥቆማዎን ያድርሱን
የሚያጋሩን ማንኛውም መልዕክት የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት ዋና ግብዓታችን ነው!
📱 9105 — መልእክትዎን ይላኩ፤ ቅሬታዎን ይፍቱ !
በቴክኒክ ብልሽት ምክንያት አገልግሎት መስጠት ያቆመውን የአዲስ ዌስት ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ትራንስፎርመር በሌላ ለመተካት የሚያስችል ተለዋጭ ትራንስፎርመር የማጓጓዝ ሥራ እየተከናወነ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ፡፡
ትራንስፎርመሩ በሚያልፍበት አካባቢ የሚገኙ የኃይል ማሥተላለፊያ መስመሮችና ድልድዮች በማጓጓዝ ሥራው ላይ እንቅፋት እንዳይሆኑ የቅየሳ ባለሙያዎች አስቀድመው ከፊት በመንቀሳቀስ መንገዶችን ምቹ የማድረግ ሥራ በመስራት ላይ ናቸው።
በማከፋፈያ ጣቢያው የሚቀየረውን ትራንስፎርመር ፈታቶ በሎውቤድ እና በሦስት አይሱዙዎች የማጓጓዝ ሥራው እየተከናወነ ይገኛል።
ትራንስፎርመሩን የጫነው ሎውቤድ በቀን በአማካይ ከ50 እስከ 70 ኪሎ ሜትር በመጓዝ ላይ ሰሆን የትራንስፎርመር ማጓጓዝ ሥራ በከፍተኛ ጥንቃቄ እየተከናወነ መሆኑን ተገልጿል፡፡
ውድ ደንበኞቻችን፤በመጓጓዝ ላይ ያለው ተለዋጭ ትራንስፎርመር በቦታው ደርሶ በኃይል ማከፋፈያ ጣቢያው ላይ ያጋጠመው የቴክኒክ ብልሽት ሲፈታ አገልግሎቱ ሙሉ በሙሉ የሚመለስ መሆኑን እየገለጽን፣ እስከዚያው ድረስ በትዕግሥት እንድትጠብቁን እየጠየቅን፤ ላሳያችሁት ትዕግሥት ከልብ እናመሰግናለን። ለተፈጠረው መስተጓጎልም ይቅርታ እንጠይቃለን።
#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
በዘመናዊው ዓለም የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት እና አስተዳደር የሀገራትን የኢኮኖሚ ዕድገት ከሚወስኑ ቁልፍ መሠረተ ልማቶች ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛል። ይህንን ወሳኝ ዘርፍ በቴክኖሎጂ በማዘመን ብክነትን መቀነስ፣ ገቢን ማሳደግ እና የደንበኞችን እርካታ ማረጋገጥ ደግሞ የየሀገራቱ የኃይል ተቋማት ዋነኛ የትኩረት አቅጣጫ ሆኗል። በዚህ ረገድ “ስማርት ኤስ.ቲ.ኤስ” (Smart STS) የቅድመ-ክፍያ ቆጣሪዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ በስፋት እየተተገበሩ ይገኛሉ።
የስታንዳርድ ትራንስፈር ስፔሲፊኬሽን ወይም ኤስ.ቲ.ኤስ (Standard Transfer Specification - STS) የቅድመ ክፍያና የስማርት ቆጣሪ ቴክኖሎጂዎች በተለይም የታዳጊ ሀገራትን የኃይል አስተዳደር በመሠረታዊነት እየቀየሩ ይገኛሉ።
በዓለም አቀፍ ደረጃ የተመዘገቡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት፤ በአሁኑ ወቅት ከ100 በላይ በሚሆኑ ሀገራት የኤስ.ቲ.ኤስ (STS) ሲስተም ተጠቃሚዎች ሲኖሩ፤ ከ75 ሚሊዮን በላይ ደንበኞች ደግሞ የዚህ ዘመናዊ አገልግሎት ተጠቃሚ እየሆኑ ይገኛሉ። በዚህ የቴክኖሎጂ ሽግግር አፍሪካውያን ሀገራት የራሳቸውን ዐሻራ ያሳረፉበት አወንታዊ ተሞክሮ አላቸው።
በተለይም ደቡብ አፍሪካ በዓለም አቀፍ ደረጃ የኤስ.ቲ.ኤስ ቅድመ-ክፍያ ቴክኖሎጂ መነሻ እና ፈር ቀዳጅ ሀገር በመሆን ትታወቃለች። በ1980ዎቹ መጨረሻ አካባቢ በሀገሪቱ የነበረውን ከፍተኛ ያልተሰበሰበ እዳ (Un collected Debt) እንዲሁም ደንበኞች በወር መጨረሻ የሚመጣባቸውን ከፍተኛ የፍጆታ ቢል የመክፈል አቅም ማነስ ችግርን በዘላቂነት ለመፍታት መንግሥት ኤስ.ቲ.ኤስ ቅድመ-ክፍያ ቆጣሪዎችን በስፋት አውሏል። አሁን ላይ በደቡብ አፍሪካ ከ10 ሚሊየን በላይ ዘመናዊ ቆጣሪዎች አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ።
በተመሳሳይ ኬንያ የኤስ.ቲ.ኤስ እና ስማርት ቆጣሪ ቴክኖሎጂዎችን በስኬት በመተግበር ከ7 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ ደንበኞቿን ተጠቃሚ አድርጋለች። ደንበኞች የሞባይል ስልካቸውን በመጠቀም በሰከንዶች ውስጥ ክፍያ ፈጽመው የኤስ.ቲ.ኤስ ቶከን ማግኘት የሚያስችላቸው አሰራር መዘርጋቱ፣ የቆጣሪ ክፍያ አሰባሰብን 99 በመቶ ስኬታማ አድርጎታል።
በኮትዲቯር ከሁለት ሚሊዮን በላይ የኤስ.ቲ.ኤስ ቆጣሪዎች ሲገጠሙ፤ ናይጄሪያ ደግሞ ለመደበኛ ደንበኞች የኤስ.ቲ.ኤስ፣ ለትላልቅ ንግድ ቤቶች የስማርት ቆጣሪዎችን አሠራጭታለች። ጋና፣ ኡጋንዳ፣ ታንዛኒያ፣ ሞሮኮና ግብፅም የዘመናዊ (AMI) ቆጣሪዎችን አገልግሎት ላይ አውለዋል። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት እነዚህን ውጤታማ ተሞክሮዎች በመውሰድ የስማርት ኤስ.ቲ.ኤስ ቆጣሪዎችን ትግበራ እያፋጠነ ይገኛል።
ከ1990 ዓ.ም በፊት ተቋሙ በዋናነት በባህላዊ (traditional me ters) ቆጣሪዎች ብቻ አገልግሎት ይሠጥ ነበር። እነዚህ ቆጣሪዎች በእጅ (በማንዋል) የሚነበቡ መሆናቸው ለቢል ንባብ ስህተት፣ ለክፍያ መዘግየት እንዲሁም ለደንበኞች ቅሬታ ዋነኛ ምክንያት ነበሩ። ከፍጆታ ንባብ ጋር ተያይዞ የሚፈጠሩ ችግሮች የደንበኞችን እምነት ከማሸርሸራቸውም በላይ፣ የተቋሙ የኤሌክትሪክ ኃይል አስተዳደር ውጤታማነት እጅግ ዝቅተኛ እንዲሆን አድርጎት ቆይቷል።
ይህን ለመቅረፍ ከ1990ዎቹ መጨረሻ አንስቶ የመረጃ ታማኝነትንና አስተዳደርን ለማሻሻል ቆጣሪዎችን የማዘመን ሥራ የተጀመረ ሲሆን፣ በ2000 ዓ.ም መጀመሪያ አካባቢ የቅድመ ክፍያ ቆጣሪዎችን ለመተግበር ሰፊ ዝግጅት ተደረገ። የቅድመ ክፍያ ሥርዓት ደንበኞች አስቀድመው ኃይል በመግዛት እንዲጠቀሙ የሚያስችል በመሆኑ፤ ከንባብ ስህተትና ከገቢ ስብሰባ ጋር ተያይዞ የነበሩ ውስንነቶችን ሊፈታ ችሏል።
ከ2012 ዓ.ም ጀምሮም ሥርዓቱን ይበልጥ ለማስፋፋት በርካታ ሥራዎች ተከናውነዋል። በአሁኑ ወቅት “የስማርት ኤስ.ቲ.ኤስ የቆጣሪ ስትራቴጂ” የሀገሪቱን የኤሌክትሪክ መሠረተ-ልማት ሙሉ በሙሉ ለማዘመን ግልጽ ዕቅድ አስቀምጧል። ከ 2025/26 እስከ 2029/30 ባለው የስትራቴጂው የትግበራ ጊዜ ተቋሙ 4 ነጥብ 15 ሚሊዮን ነባር መደበኛ ቆጣሪዎችን በዘመናዊ ቆጣሪዎች የመተካት፣ እንዲሁም 5 ሚሊዮን ስማርት ቆጣሪዎችን ለአዳዲስ ደንበኞች በመግጠም በሀገር አቀፍ ደረጃ አሁን ያለውን የአንድ ነጥብ 7 በመቶ ሽፋን ወደ 87 በመቶ ለማድረስ ታቅዷል። ይህ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ሁሉን አቀፍ ነው።
በከተማና በከፊል ከተማ ያሉ ነዋሪዎችና ኢንዱስትሪዎች የፍጆታ መረጃን በቀጥታ ለሚያስተላልፉ ስማርት ኢነርጂ ቆጣሪዎች ተጠቃሚ ሆነዋል። የቴሌኮም መሠረተ-ልማት ውስን በሆነባቸው የገጠርና ርቀት አካባቢዎች ደግሞ ነዋሪዎች በኦፍላይን ኤስ.ቲ.ኤስ (Offline STS) የቅድመ ክፍያ ቆጣሪዎች ተጠቃሚ ይሆናሉ። ስትራቴጂው ደንበኞችን እንደ ፍላጎታቸው ለይቶ ተስማሚ ቴክኖሎጂዎችን አቅርቧል። ነጠላ ፌዝ (Single Phase) ኤስ.ቲ.ኤስ ቆጣሪዎች ለመኖሪያ እና ለአነስተኛ ንግድ (እስከ 7 ነጥብ 5 ኪሎ ዋት) ያገለግላሉ።
ባለ ሦስት ፌዝ (Three Phase) ኤስ.ቲ.ኤስ ቆጣሪዎች ደግሞ ከ8-24 ኪሎ ዋት ለሚፈልጉ መካከለኛ ንግድ ቤቶችና ኢንዱስትሪዎች አገልግሎት ይሰጣሉ። በቀጣይም ከ25 እስከ 50 ኪሎ ዋት ለሚጠቀሙ ደንበኞች የሙከራ ሥራ እየተሠራ ይገኛል። የድህረ-ክፍያ ስማርት እና “DIN Split Type” የተባሉት የቅድመ ክፍያ ኤ.ኤም.አይ (AMI) ቆጣሪዎች ደግሞ ለትላልቅ የንግድ ማዕከላትና አፓርትመንቶች ይውላሉ። በሀገር አቀፍ ደረጃ ተግባራዊ እየተደረገ ያለው ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት በዓለም ባንክ የፋይናንስ ድጋፍ ኢንሄሜትር በተባለ የቻይና ኩባንያ እየተተገበረ ይገኛል።
በመጀመሪያው ዙር 350 ሺህ ነጠላ ፌዝ ኦፍላይን ቆጣሪ፣ 25 ሺህ ነጠላ ፌዝ ስማርት፣ እና 125 ሺህ ባለ ሶስት-ፌዝ ስማርት ቆጣሪዎች ይተከላሉ። ለዚህም 48 ሚሊዮን 449 ሺህ ዶላር እና 75 ሚሊየን 977 ሺህ ብር ወጪ ይደረጋል። በሁለተኛው ዙር ደግሞ 120 ሺህ ነጠላ ፌዝ ስማርት ቆጣሪ ይገጠማሉ። እ.አ.አ. ከኅዳር 11 ቀን 2023 ጀምሮ በተጀመረው ሥራ አሁን ላይ ሙሉ በሙሉ የሲስተም ትግበራው (System Inte-gration) ተጠናቆ 620 ሺህ ቆጣሪዎች አገር ውስጥ ገብተዋል።
በኮንትራክተሩ 10 ሺህ ያህሉ ሲገጠሙ፣ በተለያዩ ክልሎች ከ276 ሺህ በላይ ቆጣሪዎች ገጠማ ተከናውኗል። ከእነዚህም ውስጥ ከ236 ሺህ በላይ ኦፍላይን፣ ከ17 ሺህ በላይ ስማርት ነጠላ ፌዝ፣ እና ከ33 ሺህ በላይ ስማርት ሶስት ፌዝ ቆጣሪዎች አገልግሎት መስጠት ጀምረዋል። ከዕለት ወደ ዕለት እየጨመረ የመጣው የኤስ.ቲ.ኤስ ቆጣሪ ተጠቃሚ ደንበኛ፤ ኃይል ባለቀበት ቁጥር ወደ ማዕከል መሄድ ሳያስፈልገው፣ የሞባይል ስልኩን ብቻ በመጠቀም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (ሲቢኢ ብር)፣ በኢትዮ ቴሌኮም (ቴሌብር) እና በአዋሽ ባንክ አፕሊኬሽኖች አማካኝነት በቀን 24 ሰዓት፣ በሳምንት 7 ቀን ኃይል መሙላት የሚችልበት ምቹ እድል ተፈጥሯል።
ይህ ሰፊ ኢንቨስትመንት አድካሚ የእጅ ሥራዎችን በመቀነስ፣ትክክለኛ ቢል በማዘጋጀት፣ ገቢን በማሳደግና የኤሌክትሪክ ኃይል ብክነትን/ ስርቆትን በመቀነስ ትልቅ ድርሻ አለው። ተቋሙ ወደ ሙሉ ዲጂታላይዜሽን እየተሸጋገረ በመጣ ቁጥር፣ ሊያጋጥሙ የሚችሉ የሳይበር ጥቃቶችን (Cyber Threats) ለመከላከል ከቴክኖሎጂ ዕድገቱ ጎን ለጎን ጠንካራ የሳይበር ደኅንነት ማረጋገጫ ሥራዎችን በተጠናከረ መልኩ ለማከናወን ግልጽ ዕቅድ ተይዞ እየተሠራበት ይገኛል።