headernew2013


ERP

 erp resorse

ኢንተርፕራይዝ ሪሶርስ ፕላኒንግ ምንድን ነው?

›› የአንድን ተቋም የዕለት ተዕለት ተግባርና ኃላፊነት እንዲሁም ለዚህ የሚያስፈልገውን ሀብትና ግብዓት የሚያቀናጅ፣ የሥራ ሂደትን የሚያቀላጥፍና የመረጃ ፍሰትን የሚያሳልጥ ሰፊ የሆነ የኢንፎርሜሽን ሲስተም ነው፡፡

›› የኢ.አር.ፒ ሲስተም ማዕከላዊ/አንድ የዳታ ቋት (Centralized Database) እና ሙሉ በሙሉ በኮምፒውተር የታገዘ አሰራር ሂደትን ስለሚጠቀም ለተጠቃሚዎች ወጥ የሆነ፣ የተደራጀና ቀጣይነት ያለው የስራ ሁኔታን ይፈጥራል፡፡

›› ኢ.አር.ፒን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት መተግበር ያስፈለገበት ዋና ዋና ምክንያቶች፣ 
• የደንበንኞች አገልግሎትን ለማሳለጥ፡ 
• የሥራ አፍጻጸምንና ምርታማነትን ለማሳደግ፡ 
• መረጃ ለማቀናጀት፡ 
• የተለያዩ ስራዎችንና አሰራርን ለማቀናጀት፤ 
• ለአመራሮችና ለሰራተኞች የስራ ጫና ለማቃለል: 
• ደረጃውን የጠበቀ የስራ ግንኙነት ለመፍጠር፡ 
• ወጪን ለመቀነስ፡ 
• የተሻሻለ ቴክኖሎጂን ለመጠቀም፡ 
• ችግሮችን ፈጥኖ ለማስወገድ ስለሚረዳ ነዉ፡፡

ኢንተርፕራይዝ ሪሶርስ ፕላኒንግ /ERP/

erp resorse

በሥራ ላይ የዋለው የኢንተርፕራይዝ ሪሶርስ ፕላኒንግ የአሰራር ስርዓት እና ያስገኛቸው ጥቅሞች

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የአገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻል፣ ጥራት ያለው እና አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ለማድረግ የኢንተርፕራየዝ ሪሶርስ ፕላኒንግ የአሰራር ስርዓት ተግባራዊ ማድረጉ ይታወቃል፡፡
የአሰራር ስርዓቱ የኮንትራት ውል ስምምነቱ አጠቃላይ ወጪ የትግበራ፣ ስታንዳርድ ዋራንቲ እና የላይሰንስና የሜይንተናንስ ድጋፎችን ጨምሮ 58 ነጥብ 9 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ሲሆን፤ የገንዘብ ምንጩም የአለም ባንክ ነው፡፡
የአሰራር ስርዓቱ በአራት ምዕራፍ በሶስት ዋና ዋና ፓኬጆች ተከፍሎ በ9 የክልል ቢሮዎች እና በሁለት ከተማ መስተዳድሮች እንዲሁም በ554 በሚሆኑ የአገልግሎት መስጫ ማዕከላት ተግባራዊ ተደርጓል፡፡
በአሰራር ስርዓቱ ተግባራዊ ከተደረጉ ሞጅሎች መካከል የፋይናንስና ቁጥጥር (FICO)፣ የሰው ሀብት አስተዳደር (HCM)፣ ንብረት አስተዳደር (MM)፣ የፕሮጀክት አስተዳደር (PS/PPM)፣ ኢንተርፕራይዝ አሴት አስተዳደር (EAM) እና የጥራት አስተዳደር (QM) የደንበኞች አስተዳደር (CRM)፣ የመረጃ ግምጃ ቤት አስተዳደር (BW)፣ የመረጃ አያያዝ (DMS)፣ የሜትር ዳታ ግኝት ስርዓት (MDAS)፣ የኢነረጂ መረጃ አስተዳደር (EDM)፣ ቢሊንግና ኢንቮይስ (Billling & Invoicing)፣ የደንበኞች ኮንትራት አስተዳደር (FICA) እና ዲቫይስ/ሜትር ማናጅመነት (DM) ሞጅሎች ይገኙበታል፡፡
ተግባራዊ የተደረገው የኢንተርፕራየዝ ሪሶርስ ፕላኒንግ የአሰራር ስርዓት የተቋሙን ሃብትና ንብረት ውጤታማ በሆነ መንገድ ለመጠቀም፣ የመረጃ ልውውጡን ፈጣን፣ ወቅታዊና አስተማማኝ ለማድረግ፣ መረጃዎችን ለመሰብሰብ፣ ለማጠናቀርና ለመተንተን ከማስቻሉም በላይ የአገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሸል፣ የተቋሙን ውስጥ አሰራር ቀልጣፋ ለማድረግ፣ ቋሚና ተለዋጭ የመረጃ ቋት እንዲኖረው ለማድረግ፣ የጥሪ ማዕከል እና ሌሎች ስራዎችን ለማሻሻል ከፍተኛ አስተዋፅኦ አድርጓል፡፡
የአሰራር ስርዓቱ በገንዘብ አሰባሰብ፣ በግዥ ስርዓት፣ በንብረት አስተዳደር፣ በሰው ሃብት አስተዳደር፣ በፕሮጀክት አስተዳደር፣ በቢልና የቢል ዝግጅት፣ በመረጃ አያያዝና አስተዳደር፣ በቆጣሪ መረጃ አያያዝ፣ በጥሪ ማዕከል እና በሌሎች የተቋሙ ስራዎች ላይ ይስተዋሉ የነበሩ ችግሮችን መቅረፍ ችሏል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ በፊት በማንዋል አሰራር ይሰሩ የነበሩ ሥራዎችን ወደ አንድ ሲስተም እንዲገቡ በማድረግ የተቋሙ የስራ ሂደቶች፣ ፕሮሲጀሮች፣ ማንዋልና አጠቃላይ የመረጃ አያያዝ፣ አጠቃቀም እና ልውውጥ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፈ እንዲሆን አድርጓል፡፡
ባልተደራጀ ሁኔታ የሚሠሩ ሥራዎችን ወደ አንድ ሲስተም/ ሥርዓት እንዲገቡ በማድረግ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የታገዘ የሥራ ሂደት እንዲኖር እንዲሁም የመረጃ አያያዝ፣ ልውውጡ እና አቅርቦት ስርዓትን አስተማማኝ ማድረግ ችሏል፡፡
ፍትሃዊ የውሳኔ አሰጣጥ ስርዓት እንዲኖር እና ግልጸኝነት እንዲሰፍንም ትልቅ ድርሻ ተጫውቷል፡፡
በትግበራ ወቅት የአደረጃጀት መለዋወጥ፤ የተቋሙ መረጃዎች በሚፈለገው መልክ ተደራጅተው አለመገኘት፣ የኮሚፕዩተር ክህሎት ያለው የሰው ሃይል ማነስ፤ ስልጠና የወሰዱ ተጠቃሚዎች ሲስተሙን ተጠቅሞ ስራ ለመስራት ተነሳሽት ማነስ፤ የተወሰኑ ደንበኞች መረጃ ወደ አዲሱ ሲስተም ባለመግባቱ ቢል አለመውጣት እና የመሳሰሉ ችግሮች አጋጥመዋል፡፡
ሆኖም እነዚህ ችግሮች በአሁን ወቅት ደረጃ በደረጃ እየተፈቱ ሲሆን፤ ተቋሙ የሚሰጠውን የአገልግሎት አሰጣጥም በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘ ከማድረግ አኳያ የኢንተርፕራይዝ ሪሶርስ ፕላኒንግ የአሰራር ስርዓት ከፍተኛ ሚና እየተወጣ ይገኛል፡፡

Search