በጋምቤላ ብሄራዊ ክልል የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተደራሽ ከሆነባቸው ከተሞች መካከል ከ20 በላይ በሚሆኑ ከተሞችና የገጠር መንደሮች የሚገኘው ህብረተሰብ እስካሁን በሚፈለገው ደረጃ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ሊሆን እንዳልቻለ አቶ ቢቂላ ዋቅጂራ የክልሉ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ስራ አስፈፃሚ ጠቅሰው ህብረተሰቡ የሚፈለግበትን በማሟላት የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲሆን አሳሰቡ፡፡190166224 4376418645703548 8556154274747941814 n
ቀድሞ በነበረው ከተሞችን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተደራሽ የማድረግ አሰራር የሚያካትተው የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ግንባታ ማከናወን፣ ኮሚሽን ማድረግና ርክክብ መፈፀም እንደነበር ያስታወሱት ስራ አስፈፃሚው ህብረተሰቡ የአገልግሎት ጥያቄ ሲያቀርብና አስፈላጊውን ሲያሟላ ቀሪ ስራዎች ይከናወኑ ነበር ብለዋል፡፡
በመሆኑም በከተሞቹና በገጠር መንደሮቹ የሚገኘው ህብረተሰብ የአገልግሎት ጥያቄ ማቅረብና አስፈላጊውን ማሟላት እንዳለበት ባለመገንዘቡ እስካሁን በበቂ ሁኔታ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዳልሆነ ስራ አስፈጻሚው ገልፀዋል፡፡