የተቋሙ ከፍተኛ ሥራ አመራር የዘጠኝ ወር የዕቅድ አፈጻፀም እየገመገመ ነው

የኢትዮጵያ ኤሌክሪክ አገልግሎት ከፍተኛ ሥራ አመራር የ2013 በጀት ዓመት ያለው ዘጠኝ ወር የዕቅድ አፈፃፀም ዛሬ ሚያዝያ 13 ቀን 2013 ዓም በተቋሙ መሰብሰቢያ አዳራሽ እየገመገመ ይገኛል፡፡ በአፈፃፀም ግምገማው የተቋሙ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሽፈራው ተሊላን ጨምሮ ሁሉም የከፍተኛ ሥራ አመራር አባላት ተገኘተዋል፡፡4S5A7543

የተቋሙ ከፍተኛ ሥራ አመራር በ2013 በጀት አመት ዘጠኝ ወራት የተከናወኑ ተግባራት በጥልቀት እየገመገመ ሲሆን፤ በአፈፃፀም ወቅት የታዩ ደካማና ጠንካራ ጎኖችን እንዲሁም የዋና ዋና ግቦች አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል፡፡

ተቋሙ ባለፉት ዘጠኝ ወራት የዘመናዊ ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ከማሳደግ አንጻር በርካታ ስራዎችን ያከናወነ ሲሆን፣ የCMRI፣ የሞቶሮላ ሬዲዮ ኮሚዩኒኬሽን፣ የ905 ነጻ የጥሪ ማዕከል፣ የስካዳ ሲስተም፣ የኢንተፕራይዝ ሪሶርስ ፕላኒንግ ፕሮግራም ሞጁሎች ትግበራ፣ የቅድመ ክፍያ ሲሰተም ማሻሻል፣ የኤሌክትሪክ ማስፋፊያ ሥራዎች፣ ዲጂታል የክፍያ ስርዓት መዘርጋት፣ የሰርቪላንስ ካሜራ ተከላ እና የዲጂታል የማስታወቂያ ስራ መከናወኑን በሪፖርቱ ተመላክቷል፡፡

አዳዲስ ደንበኞችን ከማገናኘት አኳያ ባለፉት ዘጠኝ ወራት 214 ሺህ 814 ደንበኞችን ተጠቃሚ ማድረግ የተቻለ ሲሆን፤ ከባለፈው ዓመት አፈፃፀም ጋር ሲታይ 83 በመቶ ዕድገት አሳይቷል፡፡

ተቋሙ ዘመናዊ የክፍያ ስርዓቶችን የዘረጋ ሲሆን ካሉት በሲስተም ላይ ካሉት አክቲቭ  2,544,531 የድህረ ክፍያ ደንበኞች ውስጥ 27% በ ሲ ኢ ብ ር፣ 56% በቀጥታ አገልግሎት መስጫ ማዕከላት መሰብሰብ ችሏል፤ 17% የሚሆኑ ደንበኞች ደግሞ ቅድመ ክፍያ ተጠቃሚ ናቸው፡፡

በአገር አቀፍ ኤሌክትሪክ አቅርቦት ፕሮግራም በኩል የኤሌክትሪክ ተደራሽነት ከማረጋገጥ አንፃር 211 አዳዲስ ከተሞችን ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል፡፡ ይህም ከባለፈው ዓመት ጋር ሲታይ በ11.6 በመቶ ዕድገት አለው፡፡ የገጠር መንደሮችን በኦፍ ግሪድ ቴክኖሎጂ የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግ በተሰራው ስራም ከ8 ያላነሱ የገጠር መንደሮችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ መሆናቸው በሪፖርቱ ተገልጷል፡፡


Print   Email