ለሠልጣኝ ሠራተኞች የቅድመ-ቅጥር የክህሎት ስልጠና እየተሰጠ መሆኑ ተገለፀ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሰው ሃብት ስልጠናና ልማት ስራ ክፍል በቅርቡ ተቋሙን ለሚቀላቀሉ 800 ሠልጣኝ ሠራተኞች የዲስትሪቡዩሽን ቴክኒክ የክህሎት ስልጠና እየሰጠ መሆኑን የስራ ክፍሉ ሃላፊ አቶ ዳንዔል ስዩም ገልፀዋል፡፡176325571 4274912475854166 468604145903674043 n
የክህሎት ስልጠናው ከመጋቢት 13 ጀምሮ ላለፈው አንድ ወር በኮተቤ ማሰልጠኛ ማዕከል ሲሰጥ እንደቆየ የገለፁት ሃላፊው፤ ለአራት ተከታታይ ወራት የሚቀጥል በንድፈ ሃሳብና በተግባር የተደገፈ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

 እነዚህ ሠራተኞችን ከመላው ሃገሪቱ የተውጣጡ፣ ተቋሙን ለመቀላቀል ካመለከቱ 2 ሺህ 144 ተፈታኞች ውስጥ ፈተናውን አልፈው የተመረጡ እንዲሁም ከአፋር ክልል በስተቀር በሁሉም ሪጅኖችና በ22 ዲስትሪክቶች ፈተና የወሰዱ መሆናቸውን አቶ ዳንዔል አመላክተዋል፡፡176935095 4274913319187415 1964132224202981332 n176935095 4274913319187415 1964132224202981332 n176935095 4274913319187415 1964132224202981332 n

የስልጠናው ዓላማ ተቋሙን የሚቀላቀሉ አዳዲስ ሠራተኞች የተቋሙ የስራ ባህል በአግባቡ አውቀው እንዲተገብሩ ከማስቻል በተጨማሪ በንድፈ ሃሳብ ያገኙትን እውቀት በተግባራ በማስደገፍ የተሻለና ውጤታማ አገልግሎት መስጠት የሚችል ሰራተኛ ለመፍጠር፣ ሠራተኞች የቴክኒክ ስራ ጥንቃቄ የሚያስፈለገው መሆኑን ተረድተው የራሳቸውን ደህንነት እንዲጠብቁ እና ደንበኞችን ስነ-ምግባር በተሞላበት መንገድ እንዲያገለግሉ ለማስቻል መሆኑን ሃላፊው ገልፀዋል፡፡
ስልጠናው በዋናነት ትኩረት ያደረገው በኤክትሮ-መካኒካልና በዲስትርቢውሽን ቴክኒክ የስልጠና ዘርፎች ላይ መሆኑን የገለፁት ሃላፊው፤ ከተቋሙ አገልግሎት አሰጣጥ ጋር በቀጥታ ግንኙነት ያላቸው የስልጠና ዘርፎች መጨመራቸውም ተናግረዋል፡፡
የዲስትርቢውሽን ኮንስትራክሽን፣ ዲስትርቢውሽን ኢኪዩፕመንትና ሴፍቲ፣ ተቋማዊ ጤናና ሴፍቲ፣ መሰረታዊ የኤሌክትሪክ ሲፊቲ፣ ጤና እና አገልግሎት አሰጣጥ፣ የስራ ስነምግባር ለሰልጣኞች እየተሰጡ የሚገኙ የስልጠና ዘርፎች መሆናቸውንም ሃላፊው ጨምረው ገልፀዋል፡፡
ስልጠናው እየተሰጠ የሚገኘው የማሰልጠን ፍላጎትና ልምድ፣ ከስልጠናው ጋር የሚገናኝ ስራ ዘርፍ፣ የአሰልጣኞች ስልጠና ኮርስ በወሰዱ እና ሞያዊ እውቀት ባላቸው አስር የተቋሙ ሠራተኞች መሆኑን አቶ ዳንዔል ገልፀዋል፡፡
በመጀመሪያዎቹ ሁለት ወራት የስልጠና መረሃ-ግብር ውስጥ በንድፈ ሃሳብ የተደገፈ ስልጠና እንደሚሰጥና በሚቀጥሉት ሁለት ወራት ደግሞ በተግባር የተደገፈ ስልጠና እንደሆነ ሃላፊው አንሰተዋል፡፡
መሰል ስልጠናዎች የተቋሙ ሠራተኞች ችግሮቻቸውን በራሳቸው አቅም እንዲፈቱ ለማድረግ እንደሚረዳ የተናገሩት ሃላፊው፤ ተቋማዊ ለውጥ ሊያመጡ የሚችሉ የአሰራር ስርዓቶችን ተግባራዊ ለማድረግም የራሳቸውን አስተዋጾ ያበረክታሉ ብለዋል፡፡
የተቋሙ የሰው ሃብት ስልጠናና ልማት የስራ ክፍል የተቋሙን አመራርና ሰራተኞ አቅም በማሳደግ፣ የመፈፀም አቅምን ማሻሻል እና የሚስተዋሉ የአቅም ውስንነት ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችሉ ተከታታይነት ያላቸው አጫጭር፣ መካከለኛና የረጅም ጊዜ ስልጠናዎችን እየሰጠ መሆኑ ይታወቃል፡፡

Print   Email