የህፃናት ማቆያ ማዕከል ግንባታ አጠናቆ አስመረቀ
የአዲስ አበባ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሰራተኞች የህፃናት ማቆያ ማዕከል ግንባታ አጠናቆ አስመረቀ
የተቋሙ ከፍተኛ ሥራ አመራር በሩብ ዓመት የስራ አፈፃፀም ላይ ውይይት አካሄደ
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከፍተኛ ሥራ አመራር በ2014 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ከጥቅምት 11 – 12 ቀን 2014 ዓ.ም ውይይት አካሂዷል፡፡
አዲስ የገቡት የቆጣሪ መመርመሪያዎች ውጤታማ ሥራ እየሠሩ ነው ተባለ
አዲስ የገቡት የቆጣሪ መመርመሪያዎች ውጤታማ ሥራ እየሠሩ ነው ተባለ
ደንበኞች የተጠቀሙበትን ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳብ በወቅቱ ሊከፍሉ እንደሚገባ ተገለፀ
የድህረ-ክፍያ የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ደንበኞች የተጠቀሙበትን ወርሃዊ ፍጆታ ሂሳብ በወቅቱ ሊከፍሉ እንደሚገባ የዲስትሪቡሽን ሲስተም ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ብዙወርቅ ደምሴ ገልፀዋል፡፡

የሴቶችን ተሳታፊነት እና ፍትሀዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያስችል የአቅም ግንባታ ስልጠና እየተሰጠ ነው

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሴቶች፣ ህፃናት እና ወጣቶች ጉዳይ ዳይሬክቶሬት ከኮርፖሬት የሰው ሀብት ስልጠና እና ልማት ክፍል ጋር በመተባበር በስርዓተ ፆታ አካታችነት፣ በስራ አመራር እና በሴቶች ህግ ላይ ያተኮረ ስልጠና ከሚያዝያ 04 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ በሁለት ዙር ለሶስት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ በአዳማ ከተማ እየሰጠ ነው፡:setwoc1
በሁለት ዙር በሚሰጠው ስልጠና ላይ 90 የሚሆኑ ከዋናው መ/ቤት፣ ከክልል እና ከተማ አስተዳደር ኤሌክትሪክ አገልግሎት መሰረታዊ ሰራተኛ ማህበር የተውጣጡ አባላት እና የሴቶች ፣ህፃናት እና ወጣቶች ጉዳይ ስራ አስኪያጆች የሚሳተፉ ሲሆን በመጀመሪያው ዙር 40 ሰልጣኞች ተሳትፈዋል፡፡

 በመጀመሪያው ዙር የስልጠና ማጠቃለያ ላይ ተገኝተው ለሰልጣኞች መልዕክት ያስተላለፉት የኮርፖሬት ሴቶች፣ ህፃናት እና ወጣቶች ጉዳይ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ መዓዛገነት ፀጋዬ የስልጠናው ዋና ዓላማ የስርዓተ ፆታን አካታችነት ለማጎልበት፣ የሴት ሰራተኞችን የመሪነት አቅም ለማሳደግ፣ መብታቸውን ለማስከበር እና የተሰጣቸውን ሀላፊነት በአግባቡ እንዲወጡ በሚደረገው ጥረት ሰልጣኞች የድርሻቸውን እንዲወጡ ያለመ ነው ብለዋል፡፡

በተቋማችን ሴት ሰራተኞችን ለመደገፍ፣ለማብቃት እና ወደ አመራርነት ለማምጣት እየተሰራ ያለው ስራ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ያሉት ዳይሬክተሯ ስልጠናው የሰልጣኞችን እውቀት እና አመለካከት በማዳበር ተቀናጅቶ ለመስራት እና የስርዓተ ፆታ አካታችነትን ተግባራዊ ለማድረግ ወሳኝ መሆኑን አመላክተዋል፡፡
የመጀመሪያው ዙር ስልጠና ለሰልጣኞች የተሳትፎ የምስክር ወረቀት በመስጠት የተጠናቀቀ ሲሆን የሁለተኛው ዙር ስልጠና ደግሞ ከነገ ሚያዚያ 7 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ለሶስት ተከታታይ ቀናት ይቀጥላል፡፡
ዳይሬክቶሬቱ ባለፈው ግማሽ ዓመት በስራ አመራር፣ በቡድን ስራ፣ በተግባቦት እና በውሳኔ ሰጪነት ላይ ያተኮረ ስልጠና ለ201 ሴቶች እና ለ50 ወጣት ወንድ ሰራተኞች መስጠቱ የሚታወስ ነው፡፡

Print   Email