የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ስራውን በይፋ ሊጀምር መሆኑ ተገለፀ

Hits: 367

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ያልተማከለ አደራጃጀት ተግባራዊ ባደረገው መሰረት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጽ/ቤት እንዳቋቋመና ከሐምሌ 1 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ በይፋ ስራውን እንደሚጀምር ተገልጿል፡፡

000debub mirab

ይህ የተገለፀው ዛሬ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የቦርድ አባል አቶ ቦጋለ ፈለቀ፣ የአገልግሎቱ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሽፈራው ተሊላና ሌሎች የተቋሙ ከፍተኛ አመራሮች በርዕሰ መስተዳድሩ ቢሮ ባደረጉት የጋራ ስብሰባ ላይ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የቦርድ አባል አቶ ቦጋለ ፈለቀ ባደረጉት ንግግር፡- የኤሌክትሪክ አገልግሎት ጽ/ቤት በክልሉ መደራጀቱ የማህበረሰቡ ጥያቄ ለመፍታት፣ ከተደራሽነት ጋር የተያያዙ ችግሮችን ለመፍታት፣ እቅዶችን በተገቢው መንገድ ተግባራዊ ለማድረግና ያሉትን ችግሮች በጋራ ሰርቶ ምላሽ ለመስጠት፣ ተቋሙንም በባለቤትነት ለመምራትና ከህብረተሰቡ ለሚነሱ ቅሬታዎች ፈጣን ምላሽ ለመስጠት ፋይዳው የጎላ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
000debub mirab1
 
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሽፈራው ተሊላም በዚህ ወቅት፡- ቀደም ሲል በፌደራል ደረጃ በተማከለ አደረጃጀት ሲሰራበት የነበረውን አደረጃጀት ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ያልተማከለ አደረጃጀት መቀየሩን አስታውሰዋል፡፡የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በሃገር አቀፍ ደረጃ መዋቀሩን ተከትሎ እንደ ተቋምም ክልላዊ ጽ/ቤት እንዲዋቀር በቀረበው ጥያቄ መሰረት የክልሉ ኤሌክትሪክ አገልግሎት እንደ አዲስ መዋቀሩን ተናግረዋል፡፡
 
አቶ ሽፈራው አክለውም ይህም መደረጉ አገልግሎቱን ተደራሽ ለማድረግ፣ የሚሰጠውን አገልግሎት ጥራት ለማሻሻል፣ ከህብረተሰቡ ለሚነሱ ቅሬታዎች ፈጣን ምላሽ ለመስጠትና ችግሮቹን በጋራ ለመፍታት ፋይዳው የጎላ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
 
ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ በበኩላቸው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ክልሉ ላቀረበው ጥያቄ አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት ወደ ክልሉ በመምጣት ጽ/ቤቱ ስራ እንዲጀምር ላደረገው ከፍተኛ አስተዋፅኦ አመስግነዋል፡፡
ጽ/ቤቱ መቋቋሙ በክልሉ ያለውን የኤሌክትሪክ ተደራሽነት ከፍ ለማድረግ፣ ከአገልግሎት አሰጣጡ ጋር የሚነሱ ቅሬታዎችን ለመቅረፍ እና ጥራት ያለው የኤሌክትሪክ አገልግሎት ለመስጠት ጠቀሜታው ከፍተኛ መሆኑንም ጨምረው ተናግረዋል፡፡
 
ወቅታዊና ትኩስ የተቋማችን መረጃዎች ወዲያውኑ እንዲደርሳችሁ እነዚህን የትስስር ገፆቻችንን ይወዳጁ፡-
Print