የህፃናት ማቆያ ማዕከል ግንባታ አጠናቆ አስመረቀ
የአዲስ አበባ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሰራተኞች የህፃናት ማቆያ ማዕከል ግንባታ አጠናቆ አስመረቀ
የተቋሙ ከፍተኛ ሥራ አመራር በሩብ ዓመት የስራ አፈፃፀም ላይ ውይይት አካሄደ
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከፍተኛ ሥራ አመራር በ2014 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ከጥቅምት 11 – 12 ቀን 2014 ዓ.ም ውይይት አካሂዷል፡፡
አዲስ የገቡት የቆጣሪ መመርመሪያዎች ውጤታማ ሥራ እየሠሩ ነው ተባለ
አዲስ የገቡት የቆጣሪ መመርመሪያዎች ውጤታማ ሥራ እየሠሩ ነው ተባለ
ደንበኞች የተጠቀሙበትን ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳብ በወቅቱ ሊከፍሉ እንደሚገባ ተገለፀ
የድህረ-ክፍያ የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ደንበኞች የተጠቀሙበትን ወርሃዊ ፍጆታ ሂሳብ በወቅቱ ሊከፍሉ እንደሚገባ የዲስትሪቡሽን ሲስተም ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ብዙወርቅ ደምሴ ገልፀዋል፡፡

በ162 ሚሊዮን ዶላር በላይ በሆነ ወጪ የተከናወነው የማሻሻያ ፕሮጀክት ተጠናቀቀ

በአዲስ አበባ ከተማ የሚስተዋለውን የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ ችግር በዘላቂነት ለመቅረፍ በ162 ሚሊዮን ዶላር በላይ በሆነ ወጪ ሲከናወን የቆየው የማሻሻያና መልሶ ግንባታ ፕሮጀክት የፊዚካል ስራ ሙሉ በሙሉ መጠናቀቁን የፕሮጀክቱ ሃላፊ ወ/ሮ ቅድስት ላቀው ገልፀዋል፡፡

000addiababa

የመዲናዋን በፍጥነት ማደግንና የህብረተሰቡ የኃይል ፍላጎቱ ከመቼውም ጊዜ በላይ እየጨመረ መምጣቱን ተከተሎ ቀደም ሲል የነበረውን የኤሌክትሪክ መስመር እንደገና ማሻሻል አስፈላጊ ሆኖ መቆየቱን ወ/ሮ ቅድስት አንስተዋል፡፡

 

በዚህም ተቋሙ ፓወር ቻይና ከተባለ የቻይና ኩባንያ ጋር የውል ስምምነት በማድረግ የፕሮጀክቱ የሲቪል ግንባታ ሥራ በጥቅምት 2009 ዓ.ም መጀመሩን ተናግረዋል፡፡በፕሮጀክቱ 107 ነጥብ 7 ኪ.ሜ የመሬት ውስጥ ተቀባሪ የመካከለኛ መስመር ዝርጋታ፣ 69 የመካከለኛ መስመር መቆጣጠሪያ፣ ከመሬት በላይ 600 ኪ.ሜ የሚሸፍን የመካከለኛ መስመር ዝርጋታ መከናወኑን ጠቅሰዋል፡፡እንዲሁም 400 ኪ.ሜ የሚሸፍን የዝቅተኛ ቮልቴጅ መስመር ዝርጋታ፣ 61 የኮምፓክት ሰብስቴሽን እና 400 ትራንስፎርመር ተከላ ተከናውኗል ብለዋል፡፡የፕሮጀክቱ አጠቃላይ በጀት 162 ሚሊየን 168 ሺህ 370 የአሜሪካ ዶላር መሆኑን የገለፁት ሃላፊዋ፤ ከጠቅላላ ዋጋው 15 በመቶ በተቋሙ የተሸፈነ ሲሆን፤ ቀሪው 85 በመቶ ከቻይና መንግስት ኤግዚም ባንክ በተገኘ ብድር መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
የፕሮጀክቱ የፊዚካል ሥራ መቶ በመቶ ተጠናቆ በአሁን ወቅት ሙሉ ለሙሉ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡በማሰራጫ መስመሮች ላይ የሚታየውን የኃይል መቆራረጥ፣ መዋዠቅንና ኃይል ማነስ እንዲሁም የዲስትሪቢዩሽን ቴክኒካል የሆነ የኃይል ብክነትን በመቀነስ አዳዲስ ደንበኞችን ማገናኘት የሚያስችል የኔትዎርክ አቅምን ለመፍጠር በሚደረገው ጥረት ፕሮጀክቱ ሰፊ ሚና እየተጫወተ መሆኑንም አንስተዋል፡፡
በተጨማሪም ፕሮጀክቱ የተከናወነው ጥራት ባላቸው የኮንክሪት ምሰሶ፣ ሽፍን ሽቦና አስተማማኝ በሆኑ ግብዓቶች በመሆኑ የኤሌክትሪክ መቆራረጥን ከመቀነስ ባሻገር አደጋን ለመቀነስና ለመከላከል ሚና የጎላ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ወቅታዊና ትኩስ የተቋማችን መረጃዎች ወዲያውኑ እንዲደርሳችሁ እነዚህን የትስስር ገፆቻችንን ይወዳጁ፡-

Print   Email