የህፃናት ማቆያ ማዕከል ግንባታ አጠናቆ አስመረቀ
የአዲስ አበባ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሰራተኞች የህፃናት ማቆያ ማዕከል ግንባታ አጠናቆ አስመረቀ
የተቋሙ ከፍተኛ ሥራ አመራር በሩብ ዓመት የስራ አፈፃፀም ላይ ውይይት አካሄደ
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከፍተኛ ሥራ አመራር በ2014 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ከጥቅምት 11 – 12 ቀን 2014 ዓ.ም ውይይት አካሂዷል፡፡
አዲስ የገቡት የቆጣሪ መመርመሪያዎች ውጤታማ ሥራ እየሠሩ ነው ተባለ
አዲስ የገቡት የቆጣሪ መመርመሪያዎች ውጤታማ ሥራ እየሠሩ ነው ተባለ
ደንበኞች የተጠቀሙበትን ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳብ በወቅቱ ሊከፍሉ እንደሚገባ ተገለፀ
የድህረ-ክፍያ የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ደንበኞች የተጠቀሙበትን ወርሃዊ ፍጆታ ሂሳብ በወቅቱ ሊከፍሉ እንደሚገባ የዲስትሪቡሽን ሲስተም ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ብዙወርቅ ደምሴ ገልፀዋል፡፡

በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ የሴቶችን ተሳትፎ ለማሳደግ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ ነው

በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ የሴቶችን ተሳትፎ ለማሳደግ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን የሴቶች፣ ህጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ዳይሬክተር ወ/ሮ መዓዛገነት ፀጋዬ ገልፀዋል፡፡

00setyo

ዳይሬክተሯ አክለውም በተቋሙ ውስጥ የሴት ሠራተኞችን ተሳትፎና የአመራርነት ሚና ለማሳደግ እንዲቻል ከአለም ባንክ ጋር የአምስት ዓመት የስራ መርሃ ግብር በመፈራረም ሰፊ ስራዎች እየተሰሩ ነው ብለዋል፡፡

ይህንንም ከማሳካት ረገድ ቅጥር በሚፈፀምበት ወቅት ለሴቶች 50 በመቶ ኮታ፣ በውስጥ እድገትና ዝውውር ወቅት 3 በመቶ ልዩ ድጋፍ እንዲደረግ አዲስ በፀደቀው የተቋሙ የህብረት ስምምነት መፈቀዱን ተናግረዋል፡፡ተቋሙ ካሉት 4 ሺህ 886 ቋሚ ሴት ሰራተኞች መካከል 774 የሚሆኑት የመጀመሪያ ዲግሪና ከዛ በላይ ያላቸው መሆናቸውንም ጠቅሰዋል፡፡
 
ሆኖም ከእነዚህ ውስጥ በአመራርነት ላይ የተሰየሙት 222ቱ ብቻ በመሆናቸው ሴቶችን ወደ መሪነት ሚና ለማምጣት በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን አክለው ገልፀዋል፡፡
በ2014 በጀት ዓመት የሴት ሰራተኞችን አቅም ለማሳደግ፣ ብቁና ተወዳዳሪ ለማድረግ የተለያዩ ስልጠናዎች መሰጠታቸውን ዳይሬክተሯ ለማሳያ አንስተዋል፡፡
በዚህም 77 ሴት የስራ ኃላፊዎች ሊኖራቸው ስለሚገባው ተግባቦት እንዲሁም አጠቃላይ የመሪነትና ውሳኔ ሰጭነት ላይ ያተኮረ ስልጠና አግኝተዋል ብለዋል፡፡
ይህ የሴት አመራሮች ስልጠና ለሶስት አመት ቀጣይነት ያለው መሆኑንና ሰልጣኞቹ የሚለዩት በተቋሙ በሚኖራቸው ቆይታ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡
በተመሳሳይ 62 ሴት ሰራተኞች በስራቸው ውጤታማ ለማድረግ በትምህርት ዝግጁነታቸው በተፈጥሮ ሳይንስ እና በማህበራዊ ሳይንስ ተከፍለው የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና እንደተሰጣቸው ተናግረዋል፡፡
በበጀት ዓመቱ በአጠቃላይ ለ564 ሴት አመራርና ሰራተኞች የክህሎትና አቅም ማሳደግ ስልጠና እንዲሁም በተለያዩ መድረኮች በመገኘት 551 ለሚሆኑ ሰራተኞች ስርዓተ ፆታን የተመለከተ የግንዛቤ ማስጨበጫ መስጠት መቻሉንም አንስተዋል፡፡
በተጨማሪም ለ42 ሴቶች የሁለተኛ ዲግሪ የነፃ የትምህርት እድል የተመቻቸ መሆኑን ያነሱት ዳይሬክተሯ፤ በአሁን ሰዓት በአጠቃላይ 88 ሴቶች የሁለተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ እንደሆነም ገልፀዋል፡፡
ሌላው በበጀት አመቱ ከተሰሩ ስራዎች ውስጥ የህፃናት ማቆያ አገልግሎት ተጠቃሽ ሲሆን፤ በዚህ ዓመት በተለያዩ አካባቢዎች ደረጃቸውን የጠበቁ 9 የህፃናት ማቆያዎች ተከፍተው አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
ይህም ሴት ሠራተኞችን በስራ ላይ የሚኖርባቸውን ጫና ለማቃለልና ውጤታማ እንዲሆኑ በማሰብ ተቋሙ ከአለም ባንክ ጋር በመተባበር ያመቻቸው ዕድል መሆኑን ጨምረው ጠቁመዋል፡፡
ወቅታዊና ትኩስ የተቋማችን መረጃዎች ወዲያውኑ እንዲደርሳችሁ እነዚህን የትስስር ገፆቻችንን ይወዳጁ፡-

Print   Email