የህፃናት ማቆያ ማዕከል ግንባታ አጠናቆ አስመረቀ
የአዲስ አበባ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሰራተኞች የህፃናት ማቆያ ማዕከል ግንባታ አጠናቆ አስመረቀ
የተቋሙ ከፍተኛ ሥራ አመራር በሩብ ዓመት የስራ አፈፃፀም ላይ ውይይት አካሄደ
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከፍተኛ ሥራ አመራር በ2014 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ከጥቅምት 11 – 12 ቀን 2014 ዓ.ም ውይይት አካሂዷል፡፡
አዲስ የገቡት የቆጣሪ መመርመሪያዎች ውጤታማ ሥራ እየሠሩ ነው ተባለ
አዲስ የገቡት የቆጣሪ መመርመሪያዎች ውጤታማ ሥራ እየሠሩ ነው ተባለ
ደንበኞች የተጠቀሙበትን ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳብ በወቅቱ ሊከፍሉ እንደሚገባ ተገለፀ
የድህረ-ክፍያ የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ደንበኞች የተጠቀሙበትን ወርሃዊ ፍጆታ ሂሳብ በወቅቱ ሊከፍሉ እንደሚገባ የዲስትሪቡሽን ሲስተም ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ብዙወርቅ ደምሴ ገልፀዋል፡፡

በተለያዩ ተቋማት የሚሰሩ ግንባታዎች በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶች ላይ የሚያደርሱት ጉዳት እየጨመረ ነው

በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ መንግስታዊና መንግስታዊ ባልሆኑ ተቋማት የሚሰሩ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች ከመሬት በታች በተቀበሩ የኤሌክትሪክ መስመሮች ላይ ጉዳት እያደረሱ መሆኑን የደቡብ እና ምዕራብ አዲስ አበባ ዲስትሪክቶች አስታወቁ፡፡

000ika

በቸልተኝነትና በጥንቃቄ ጉድለት በሚሰሩ ስራዎች ምክንያት በከፍተኛና በመካከለኛ የኤለክትሪክ ተሸካሚ መስመሮች ላይ የሚደርሰው ጉዳት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱ በተቋሙና በደንበኞች ላይ አሉታዊ ተፅዕኖው የጎላ መሆኑን ተጠቅሷል፡፡

የደቡብ አዲስ አበባ ዲስተሪክት ዳይሬክተር አቶ ጂሳ ካሳ እንደገለፁት በተለያዩ ተቋማት የሚሰሩ የግንባታ ስራዎች ጋር ተያይዞ በኤሌክትሪክ መስመሮች ላይ የሚደርሰው ጉዳት በሚያስከትለው የኤሌክትሪክ መቆራረጥ ከደንበኞቹ ቅሬታ ከማስነሳቱ በተጨማሪ ተቋሙን ላልተፈለገ ወጪ እየዳረገው ይገኛል፡፡በያዝነው በጀት ዓመት በቃሊቲና በለቡ አደባባይ አካባቢ በመሬት ውስጥ በተቀበሩ የኤሌክትሪክ አስተላላፊ መስመሮች ላይ በመንገድ ስራ ምክንያት አደጋ መድረሱን የጠቀሱት አቶ ጂሳ፤ በዚህም ከ11 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት 4 ሺህ 500 ሜትር የኤሌክትሪክ ገመድ ወድሟል ብለዋል፡፡
ይህን ተከትሎ መሰል ጉዳቶች ሲከሰቱ ለተጎዱት መስመሮች ጊዜያዊና ዘላቂ መፍትሄዎች በመስጠት በአካባቢዎቹ አገልግሎቱን በፍጥነት ለመመለስ ጥረት እንደሚደረግ አቶ ጂሳ ጠቅሰዋል፡፡
በተመሳሳይ በምዕራብ አዲስ አበባ ዲስትሪክት 10 በመሬት ላይ የተቀበሩ ከፍተኛ ወጪ የወጣባቸው የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶች ላይ ጉዳት መድረሱን በዲስትሪክቱ የዲስትሪቢውሽን፣ ኮንስትራክሽንና ሚይንቴናንስ ስራ አስኪያጅ አቶ አህመድ ሀሺም ገልፀዋል፡፡
ቴሌ ጋራጅ፣ ሜክሲኮ ቡናና ሻይ፣ አየር ጤና አደባባይ፣ አፍሪካ ህብረት አደባባይ እና ካዛንችስ ሀናን ዳቦ ቤት አካባቢዎች ጉዳቱ ከደረሰባቸው መካከል የሚጠቀሱ ሲሆን፣ ጉዳቱ የደረሰው በአዲስ አበባ መንገድ ስራዎች፣ በኢትዮ ቴሌኮም እና በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲስ የህንፃ ግንባታ መሆኑን አቶ አህመድ አስታውቀዋል፡፡ይህንን ተከትሎ በእነዚህ አካባቢዎች በደረሰው ጉዳት ተቋሙ 11 ሚሊዮን 920 ሸህ 249 ብር ያጣ መሆኑን አቶ አህመድ ጠቅሰው፤ የደረሰውን ኪሳራ ተቋማቱ በህግ አግባብ እንዲከፍሉ ይደረጋል ብለዋል፡፡
 
ሆኖም ያደረሱትን የጉዳት መጠን በወቅቱ የሚከፍሉ ተቋማት እንዳሉ ሁሉ ክፍያውን በወቅቱ የማይፈፅሙ ተቋማት እንዳሉ አቶ አህመድ ገልፀው፤ ለአብነትም በአዲሱ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ህንጻ ግንባታ በደረሰው ከ3 ሚሊየን 50 ሺህ ብር በላይ የሚገመት ጉዳት ክፍያው እስካሁን ባለመፈፀሙ ጉዳዩ በህግ መያዙን አብራርተዋል፡፡
በግንባታው ዘርፍ የተሰማሩ የግልም ሆነ የመንግስት ተቋማት ለሚሰሯቸው የመሰረተ ልማት ግንባታዎች ቁፋሮ በሚያከናውኑበት ወቅት ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጋር በመናበብ መስራት እንደሚገባ አቶ አህመድ አስገንዝበዋል፡፡
በመሰረተ ልማት ቅንጅት ቢሮ በኩል የተዘጋጀ የጋራ መግባባያ ሰነድ ቢኖርም የልማት ተቋማቱ ህጉንና ስምምነቱን ጠብቀው እየሰሩ ባለመሆኑ ተቋሙን ላልተፈለገ ወጪ ከመዳረጉ በተጨማሪ ለሌሎች ስራዎች የሚያወጣውን አቅርቦትና ጊዜ በመልሶ ጥገና እንዲያባክን አድርጎታል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
በመሆኑም የመሰረተ ልማት ቅንጅት ቢሮ ያፈራረመውን ስምምነት መሰረት በማድረግ ስራዎች በተገቢው መንገድ እንዲሰሩ ክትትል ማድረግ፣ መቆጣጠርና ስምምነቱን በጣሱ ተቋማት ላይ ተገቢውን እርምጃ መውሰድ አለበት ብለዋል፡፡
ከመሰረተ ልማት ግንባታዎች ጋር ተያይዞ በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶች ላይ የሚደርሰው ጉዳት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መሆኑ በአገልግሎት አሰጣጥ ጥራት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እያሳደረ ሲሆን፤ ከደንበኞች ቅሬታ እያስነሳ መሆኑን የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡
በ2014 ዓ.ም በጀት ዓመት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በደቡብና ምዕራብ አዲስ አበባ ዲስተሪክቶች ብቻ በአጠቃላይ ወደ 24 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ የመሰረተ ልማት ጉዳት ደርሶበታል፡፡
ሆኖም ይህ በማሳያነት ተጠቀሰ እንጂ በሌሎች የሃገሪቱ አካባቢዎችም መሰል ጉዳቶች በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶች ላይ እየደረሱ ሲሆን፤ ይህም ለተደጋጋሚ የኤሌክትሪክ መቋረጥና መዋዥቅ መንስኤ እየሆነ ይገኛል፡፡
ወቅታዊና ትኩስ የተቋማችን መረጃዎች ወዲያውኑ እንዲደርሳችሁ እነዚህን የትስስር ገፆቻችንን ይወዳጁ፡-

Print   Email