በወሩ ከ22 ሺህ በላይ አዳዲስ ደንበኞች የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ተደርገዋል

Hits: 128

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ባሳለፍነው ግንቦት ወር ከ22 ሺህ በላይ አዳዲስ ደንበኞችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ማድረግ ችሏል፡፡

00EEU

በአጠቃላይ በወሩ 26 ሺህ 516 ደንበኞች ተጠቃሚ የሆኑ ሲሆን፤ ከእነዚህም ውስጥ 96 ከመቶ የድህረ-ክፍያና 4 በመቶ የሚሆኑት የቅድመ-ክፍያ አገልግሎት ተጠቃሚ ናቸው፡፡

ፍትሃዊ የኤሌክትሪክ ተደራሽነትን እውን ለማድረግ በተሰራው ሥራ በግንቦት ወር ብቻ 17 የገጠር ከተሞችና መንደሮች የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ማድረግም ተችሏል፡፡እነዚህን ከተሞችና መንደሮች ተጠቃሚ ለማድረግ ተቋሙ 236 ነጥብ 88 ኪሎ ሜትር የመካከለኛ መስመር እንዲሁም 163 ነጥብ 25 ኪሎ ሜትር የዝቅተኛ የኤሌክትሪክ መስመር ዘርግቷል፡፡
 
በተቋሙ የሚሰሩ ስራዎችን በሶስተኛ ወገን ከማሰራት አንጻር በግንቦት ወር ለ1 ሺህ 426 ዜጎች ቋሚና ጊዜያዊ የሥራ እድል ተፈጥሯል፡፡በወሩ ለተቋሙ ከቀረቡና በዘመናዊ ሲስተም ተመዝግበው ከነበሩት 26 ሺህ 780 የደንበኞች ቅሬታዎች መካከል 20 ሺህ 453 የሚሆኑት ምላሽ ያገኙበትም ነው፡፡
 
ዘመናዊ ቴክኖሎጂን ከመተግበር አንፃር የቅድመ-ክፍያ ቆጣሪ ሲስተምን ከ500 ባላነሱ የአገልግሎት መስጫ ማዕከላት ላይ መሰረተ-ልማቱን የማስፋፋት ስራ ተከናውኗል፡፡ከሥነ ምግባርና ብልሹ አሰራሮች ጋር የተገናኙ ከደንበኞች 19 አቤቱታዎች ቀረበው 17ቱ መፍትሄ አንዲያገኙም ተደርጓል፡፡
 
የተቋሙን የሰው ሐብት ውጤታማነትን ከማሳደግ አኳያ በወሩ ለ186 ወንድና ለ214 ሴት በድምሩ ለ400 ሠራተኞች በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ስልጠና ማግኘታቸውን የኮርፖሬት ፕላኒነግና ሪፖርቲንግ ዳይሬክቶሬት መረጃ ያመለክታል፡፡
ወቅታዊና ትኩስ የተቋማችን መረጃዎች ወዲያውኑ እንዲደርሳችሁ እነዚህን የትስስር ገፆቻችንን ይወዳጁ፡-
Print