የህፃናት ማቆያ ማዕከል ግንባታ አጠናቆ አስመረቀ
የአዲስ አበባ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሰራተኞች የህፃናት ማቆያ ማዕከል ግንባታ አጠናቆ አስመረቀ
የተቋሙ ከፍተኛ ሥራ አመራር በሩብ ዓመት የስራ አፈፃፀም ላይ ውይይት አካሄደ
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከፍተኛ ሥራ አመራር በ2014 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ከጥቅምት 11 – 12 ቀን 2014 ዓ.ም ውይይት አካሂዷል፡፡
አዲስ የገቡት የቆጣሪ መመርመሪያዎች ውጤታማ ሥራ እየሠሩ ነው ተባለ
አዲስ የገቡት የቆጣሪ መመርመሪያዎች ውጤታማ ሥራ እየሠሩ ነው ተባለ
ደንበኞች የተጠቀሙበትን ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳብ በወቅቱ ሊከፍሉ እንደሚገባ ተገለፀ
የድህረ-ክፍያ የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ደንበኞች የተጠቀሙበትን ወርሃዊ ፍጆታ ሂሳብ በወቅቱ ሊከፍሉ እንደሚገባ የዲስትሪቡሽን ሲስተም ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ብዙወርቅ ደምሴ ገልፀዋል፡፡

ሁለተኛው የህብረት ስምምነት ተፈረመ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከተቋሙ መሰረታዊ ሠራተኛ ማህበር በጋራ በመሆን ለሁለተኛው ጊዜ ያዘጋጁትን የሠራተኞች ህብረት ስምምነት  ሰኔ 8 ቀን 2014 ዓ.ም ተፈርሟል፡፡

000hibretsimmenet

የህብረት ስምምነቱን የፈረሙት የተቋሙ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሽፈራው ተሊላ እና የመሰረታዊ ሠራተኛ ማህበር ሊቀመንበር አቶ ሃይሉ ዘውዴ ናቸው፡፡

ለሁለተኛ ጊዜ እንደገና የተሻሻለው ይህ የህብረት ስምምነት፤ በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 ዓ.ም መሰረት መሆኑን የሰው ሃብት አስተዳደርና ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ዘሪቱ ፍቅሬ ገልፀዋል፡፡የህብረት ስምምነቱ የተቋሙን፣ የሠራተኛውንና የደንበኛውን ጥቅም ባስጠበቀ መልኩ ሥራዎች ለማከናወንና ሰራተኛው መብትና ግዴታውን አውቆ እንዲሰራ ለማድረግ የሚረዳ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
 
ዳይሬክተሯ አክለውም በተሻሻለው የህብረት ስምምነት ከተካተቱ አንቀፆች መካከል ከሰኞ እስከ አርብ ብቻ የነበረውን የሥራ ቀን እስከ ቅዳሜ ግማሽ ቀን ድርስ የተራዘመ ሲሆን፤ በዚህም ጥራት ያለውና አስተማማኝ አገልግሎት ለመስጠትና የደንበኞችን የእርካታ ደረጃ ከፍ ለማድረግ ታሳቢ ያደረገ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
 
የመሰረታዊ ሰራተኛ ማህበር ሊቀመንበር አቶ ሃይሉ ዘውዴ በበኩላቸው የህብረት ስምምነቱን ማሻሻል ያስፈለገው የመጀመሪያው ስምምነት የአራት ዓመት የቆይታ ጊዜው በመጠናቀቁና ለአሰራር ምቹ ያልሆኑ አንቀጾችን ለማሻሻል፣ ሰራተኞችንና ደንበኞችን ተጠቃሚ ሊያደርጉ የሚችሉ ተጨማሪ አንቀጾችን ለማካተት ታስቦ መሆኑን ገልፀዋል፡፡በዚህም ለተቋሙ ደንበኞችና ሠራተኞች ተጠቃሚ የሚያደርጉ በርካታ አንቀፆች መሻሻላቸውንና መጨመራቸውን አስታውቀዋል፡፡
 
አቶ ሃይሉ አክለውም በዚህ ህብረት ስምምነት በበፊቱ በግልፅ ተለይተው ያልተቀመጡ የስራ መስሪያና የስራ ላይ ደህንነት መጠበቂያ ቁሣቁሶች መቀመጣቸውን፣ ሃላፊነቱን በአግባቡ በማይወጣ ሰራተኛ ላይ ስለሚወሰዱ የተጠያቂነት ስርዓት፣ ስለሚያገኙት ጥቅማ ጥቅም ጨምሮ ሌሎች ጉዳዮችን የሚመለከቱ አንቀፆች ተካተዋል ብለዋል፡፡
 የተፈረመው የህብረት ስምምነት ለቀጣይ አራት አመታት አንደሚያገለግል በፊረማ ስነ ስርዓቱ ላይ ተገልጿል፡፡
ወቅታዊና ትኩስ የተቋማችን መረጃዎች ወዲያውኑ እንዲደርሳችሁ እነዚህን የትስስር ገፆቻችንን ይወዳጁ፡-

Print   Email