የህፃናት ማቆያ ማዕከል ግንባታ አጠናቆ አስመረቀ
የአዲስ አበባ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሰራተኞች የህፃናት ማቆያ ማዕከል ግንባታ አጠናቆ አስመረቀ
የተቋሙ ከፍተኛ ሥራ አመራር በሩብ ዓመት የስራ አፈፃፀም ላይ ውይይት አካሄደ
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከፍተኛ ሥራ አመራር በ2014 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ከጥቅምት 11 – 12 ቀን 2014 ዓ.ም ውይይት አካሂዷል፡፡
አዲስ የገቡት የቆጣሪ መመርመሪያዎች ውጤታማ ሥራ እየሠሩ ነው ተባለ
አዲስ የገቡት የቆጣሪ መመርመሪያዎች ውጤታማ ሥራ እየሠሩ ነው ተባለ
ደንበኞች የተጠቀሙበትን ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳብ በወቅቱ ሊከፍሉ እንደሚገባ ተገለፀ
የድህረ-ክፍያ የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ደንበኞች የተጠቀሙበትን ወርሃዊ ፍጆታ ሂሳብ በወቅቱ ሊከፍሉ እንደሚገባ የዲስትሪቡሽን ሲስተም ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ብዙወርቅ ደምሴ ገልፀዋል፡፡

እስካሁን 227 ስማርት የኤሌክትሪክ ቆጣሪ መቀየር መቻሉን ተገለፀ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የ50 ሺህ የከፍተኛ ሃይል ተጠቃሚ ደንበኞች ነባር የኤሌክትሪክ ቆጣሪ በዘመናዊ ስማርት ቆጣሪዎች የመተካት ስራ እያከናወነ መሆኑን ይታወቃል፡፡

00tekeyere

ዘመናዊ ቆጣሪዎቹ ከዚህ ቀደም የነበሩ የንባብ ክፍተቶችን የሚያሻሽሉና ዘመኑ የደረሰበትን ቴክኖሎጂ የሚጠቀሙ ናቸው፡፡

ነባር ቆጣሪዎችን በአድቫንስድ ሜትሪንግ ኢንፍራስትራክቸር ወይም ስማርት ሜትር የመቀየር ስራው የተጀመረው ከመጋቢት 2014 ዓ.ም ጀምሮ ሲሆን፤ እስካሁን 227 ስማርት የኤሌክትሪክ ቆጣሪ መቀየር መቻሉን የአድቫንስድ ሜትሪንግ ኢንፍራስትራክቸርና ስካዳ ፕሮጀክት ኃላፊ አቶ ጩመላ ሳሙኤል ገልፀዋል፡፡እየተቀየረ የሚገኘው ቆጣሪ ዘመኑን የዋጀና የረቀቀ በመሆኑ ከቆጣሪ መረጃ የሚወሰደው በውስጡ በሚገጠም ሲምካርድ አማካኝነት መሆኑንና ተቋሙ ከተገበረው ሳፕ /SAP/ ሲስተም ጋር መረጃዎችን በመለዋወጥ ለደንበኛ ቢል በወቅቱ እንዲዘጋጅ ያግዛል ብለዋል፡፡
 
ሲምካርዱ ከኢትዮ ቴሌኮም የሚወሰድ መሆኑን የጠቆሙት ኃላፊው፤ በተሰጠው የሰዓት ልዩነት የፍጆታ ንባቦችን፣ የኃይል መቋረጥና መዋዠቆች፣ የቆጣሪ መከፈትና የባትሪ አለመስራት መረጃዎችን ወደ ተቋሙ የመረጃ ቋት እንደሚልክ ተናግረዋል፡፡አቶ ጩመላ እንደገለፁት ደንበኛ የሞባይል መተግበሪያን በመጠቀም የራሳቸውን ወርሃዊ የኃይል ፍጆታ መከታተል ስለሚያስችል፤ የቤት ለቤት ንባብም ሆነ የንባብ ስህተትን ያስቀራል፣ በወቅቱ ንባብ ባለመውሰድ የሚፈጠር ውዝፍ እዳ ባልታሰበ ጊዜ ከመክፈል እንደሚታደግ ገልፀዋል፡፡
 
በተቋሙ በኩልም ገንዘብ በወቅቱ ለመሰብሰብ ከማስቻሉ በተጨማሪ ቆጣሪ ከተነካካ መረጃ ወደ መቆጣጠሪያ ማዕከል በመላክ የኤሌክትሪክ ኃይል ስርቆትን ይከላከላል፤ በእጅ የሚሠራ የቆጣሪ ንባብን እንደሚያስቀር ጠቁመዋል፡፡
 
ስማርት ሜትሩ የኃይል ስርቆትን ለመከላከል የሚያስችል፣ የደንበኛ ቅሬታ የሚቀንስ፣ ደንበኛው ወቅቱን ጠበቆ ወርሃዊ ክፍያ እንዲፈፅምና ትክክለኛ መረጃ እንዲያገኝ ለማድረግ የሚስችል፣ የንባብ ስህተት ችግርን የሚቀርፍ፣ የኃይል መቆራረጥ ችግር ሲፈጠር በማዕከል ደረጃ መፍትሄ ለመስጠትና ሌሎች ችግሮችን በቀላሉ ለመከላከል የሚስችል መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
 
ሆኖም ፕሮጀክቱ በታሰበው ጊዜና ዕቅድ መሰረት ለማጠናቀቅ እነዚህ ከፍተኛ ኃይል የሚጠቀሙ የኢንዱስትሪ ደንበኞች እየተቀየር የሚገኘው ስማርት ሜትር ጠቀሜታ ተረድተው ለአፈፃፀሙ ተገቢውን እገዛ ማድረግ እንደሚገባቸው ገልፀዋል፡፡
 
ነባር ቆጣሪዎችን በአድቫንስድ ሜትሪንግ ኢንፍራስትራክቸር ወይም ስማርት ሜትር የመቀየር ስራው ለደንበኞች የሚያስገኘውን ጠቀሜታ እጅግ የላቀ መሆኑን ተረድተው፤ ቆጣሪ ለመቀየር የተቋማችን ባለሞያዎች ሲመጡ የሚጠየቁትን መረጃ በቶሎ መስጠት እንዲሁም ሌሎች የሚጠየቁትን አስፈላጊ ትብብሮችን በማድረግ ለፕሮጀክቱ ስኬት የራሳቸውን እገዛ መወጣት እንደሚገባቸው ኃላፊው አሳስበዋል፡፡
አድቫንስድ ሜትሪንግ ኢንፍራስትራክቸር ፕሮጀክት ከአለም ባንክ በተገኘ 12 ሚሊየን 546 ሺህ 54 ዶላር ድጋፍና በተቋሙ 9 ሚሊየን 640 ሺህ 450 ብር በጀት ኑሪፍሌክስ በተባለ ኃላፊነቱ የተወሰነ የኮሪያ ኩባንያ የቆጣሪ ቅየራ ስራው እየተከናወነ መሆኑን አቶ ጨመላ አክለው አስታውቀዋል፡፡
 
በፕሮጀክቱ የመጀመሪያ ምዕራፍ 5 ሺህ ቆጣሪዎችን የመቀየር ስራ በኮንትራክተሩ በኩል እንደየተሰራ መሆኑን የገለፁት ኃላፊው፤ በሁለተኛው ምዕራፍ 45 ሺህ ቆጣሪዎችን በራስ ዓቅም ይቀየራሉ ብለዋል፡፡
ወቅታዊና ትኩስ የተቋማችን መረጃዎች ወዲያውኑ እንዲደርሳችሁ እነዚህን የትስስር ገፆቻችንን ይወዳጁ፡-

Print   Email