የህፃናት ማቆያ ማዕከል ግንባታ አጠናቆ አስመረቀ
የአዲስ አበባ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሰራተኞች የህፃናት ማቆያ ማዕከል ግንባታ አጠናቆ አስመረቀ
የተቋሙ ከፍተኛ ሥራ አመራር በሩብ ዓመት የስራ አፈፃፀም ላይ ውይይት አካሄደ
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከፍተኛ ሥራ አመራር በ2014 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ከጥቅምት 11 – 12 ቀን 2014 ዓ.ም ውይይት አካሂዷል፡፡
አዲስ የገቡት የቆጣሪ መመርመሪያዎች ውጤታማ ሥራ እየሠሩ ነው ተባለ
አዲስ የገቡት የቆጣሪ መመርመሪያዎች ውጤታማ ሥራ እየሠሩ ነው ተባለ
ደንበኞች የተጠቀሙበትን ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳብ በወቅቱ ሊከፍሉ እንደሚገባ ተገለፀ
የድህረ-ክፍያ የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ደንበኞች የተጠቀሙበትን ወርሃዊ ፍጆታ ሂሳብ በወቅቱ ሊከፍሉ እንደሚገባ የዲስትሪቡሽን ሲስተም ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ብዙወርቅ ደምሴ ገልፀዋል፡፡

ማዕከሉ ክረምት ከመግባቱ በፊት የቅድመ ጥገና ስራዎች እየሰራ ነው

በክረምት ወቅት የኤሌክትሪክ መቆራረጥን ለመከላከል ጥገናና ማሻሻያ የሚያስፈልጋቻው የኤሌክትሪክ መስመሮችን በመለየት የማሻሻያና የቅድመ ጥገና ስራዎች እየተሰራ መሆኑን የአርሲ ነጌሌ አገልግሎት መስጫ ማዕከል አስታውቋል፡፡

00nagele arsi

የማዕከሉ ሥራ አስኪያጅ አቶ ሳምሶን ሰንበቶ እንደገለፁት የማሻሻያና ጥገና ስራው አስቀድሞ የተጀመረና የመኖሪያ ቤትን ጨምሮ የከፍተኛ ኃይል ተጠቃሚ ኢንዱስትሪዎችን ተጠቃሚ አድርጓል፡፡

ለዚህም ማሳያ በአርሲ ነጌሌ ከተማ የሚገኘው የግንድ መሰንጠቂያና የጣውላ ማምረቻ አንዱ ነው ብለዋል፡፡በኦሮሚያ ደንና እንስሳት ድርጅት የአርሲ ቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጅ አቶ ገበየው ዘለቀ በበኩላቸው ማዕከሉ ባከናወነው የማሻሻያ ሥራ የማምረቻው የኃይል ዕጥረት መፈታቱንና በሙሉ አቅሙ እንዲያመርት ማስቻሉን ተናግረዋል፡፡የጣውላ ማምረቻው ከዚህ ቀደም በኃይል እጥረት ምክንያት ምርቱ የተወሰነ እንደ ነበረና የአርሲ ነገሌ አገልግሎት መስጫ ማዕከል በሰጠው ፈጣን ምላሽና በተደረገው የኃይል አቅርቦት ማሻሻያ ፋብሪካው በሙሉ አቅሙ ወደ ስራ እንዲገባ አስችሎታል ብለዋል፡፡
 
ፋብሪካው ከፍተኛ ኃይል የሚጠቀሙ ማሽኖችን የሚጠቀም መሆኑን የጠቀሱት ስራ አስኪያጁ፤ ቀደም ሲል ነዳጅ በሚጠቀምበት ወቅት በድርጅቱ ምርት ላይ አሉታዊ ጫና ከመፍጠሩ በተጨማሪ ማምረቻው ለከፍተኛ ወጪ ሲጋለጥ መቆየቱን አንስተዋል፡፡አሁን ላይ የኃይል አቅርቦቱ በመሻሻሉ ፋብሪካው ስራውን በቅልጥፍና እንዲከናወን ከማስቻሉም በተጨማሪ የድርጅቱ ምርት መጨመሩን የገለፁት አቶ ገበየው፤ ማዕከሉ ለሰጠው ፈጣን ምላሽ አመስግነዋል፡፡
 
የማሻሻያና የጥገና ሥራዎችን ከመስራት ጎን ለጎን ደንበኞች ዘመናዊ የክፍያ አማራጮችን ተጠቅመው ወርሃዊ የፍጆታ ሂሳባቸውን እንዲከፍሉ እየተሰራ መሆኑን የአርሲ ነጌሌ አገልግሎት መስጫ ማዕከል ሥራ አስኪያጅ አቶ ሳምሶን ሰንበቶ ገልጸዋል፡፡
በዚህም አሁን ላይ ከግማሽ በላይ የሚሆኑ የማዕከሉ ደንበኞች በዘመናዊ አማራጮችን በመጠቀም ወርሃዊ የኤሌክትሪክ የፍጆታ ሂሳብ ክፍያ እየፈፀሙ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡ነገር ግን ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ክፍያቸውን በወቅቱ የማይፈፅሙ እና ቆጣሪ አንባቢዎችን ቤት አትገቡም በማለት የማስፈራራት ተግባር የሚፈፅሙ አንዳንድ ደንበኞች መኖራቸውን አቶ ሳምሶን ጠቁመው፤ ይህ አይነቱን ችግር ለመፍታት ማዕከሉ ከህብረተሰቡ፣ ከከተማው አስተዳደር፣ ከሰላምና ፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
 
ደንበኞችም ተቋሙ ለሚሰጣቸው አገልግሎት መክፈል ያለባቸውን ወርሃዊ ክፍያ በወቅቱና በአግባቡ መፈፀም እንዳለባቸው በመጥቀስ፤ ለቆጣሪ አንባቢዎችና ለሌሎች የተቋሙ ሠራተኞች የሚጠበቅባቸው ትብብር እንዲያደረጉም ጠይቀዋል፡፡
ወቅታዊና ትኩስ የተቋማችን መረጃዎች ወዲያውኑ እንዲደርሳችሁ እነዚህን የትስስር ገፆቻችንን ይወዳጁ፡-

Print   Email