የህፃናት ማቆያ ማዕከል ግንባታ አጠናቆ አስመረቀ
የአዲስ አበባ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሰራተኞች የህፃናት ማቆያ ማዕከል ግንባታ አጠናቆ አስመረቀ
የተቋሙ ከፍተኛ ሥራ አመራር በሩብ ዓመት የስራ አፈፃፀም ላይ ውይይት አካሄደ
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከፍተኛ ሥራ አመራር በ2014 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ከጥቅምት 11 – 12 ቀን 2014 ዓ.ም ውይይት አካሂዷል፡፡
አዲስ የገቡት የቆጣሪ መመርመሪያዎች ውጤታማ ሥራ እየሠሩ ነው ተባለ
አዲስ የገቡት የቆጣሪ መመርመሪያዎች ውጤታማ ሥራ እየሠሩ ነው ተባለ
ደንበኞች የተጠቀሙበትን ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳብ በወቅቱ ሊከፍሉ እንደሚገባ ተገለፀ
የድህረ-ክፍያ የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ደንበኞች የተጠቀሙበትን ወርሃዊ ፍጆታ ሂሳብ በወቅቱ ሊከፍሉ እንደሚገባ የዲስትሪቡሽን ሲስተም ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ብዙወርቅ ደምሴ ገልፀዋል፡፡

ማዕከሉ 1 ሺህ 950 ደንበኞችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ አደረገ

የገላን ከተማ አገልግሎት መስጫ ማዕከል በዘጠኝ ወራት ውስጥ ለ1 ሺህ 950 አዳዲስ ደንበኞችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ማድረጉን የማዕከሉ ስራ አስኪያጅ አቶ አለምዘውድ በቀለ አስታውቀዋል፡፡

0galan

አዲስ ኃይል ከተገናኘላቸው ደንበኞች ውስጥ 10 የሚሆኑት የኢንዱስትሪ ደንበኞች መሆናቸውን የገለፁት አስኪያጁ፤ በአቅርቦት ችግር ምክንያት ለረዥም አመታት ከፍለው ሲጠባበቁ የነበሩ ደንበኞች ናቸው ብለዋል፡፡

ሆኖም በራሳቸው አቅም የሚያስፈልገውን ግብዓት ለሚያቀርቡ ደንበኞች የጥራት መመዘኛውን በመስጠትና ከተገዛ በኋላም ጥራቱን በመፈተሸ ሳምንት በማይሞላ ጊዜ አገልግሎቱ እየተሰጠ መሆኑን አቶ አለምዘውድ ጠቅሰዋል፡፡ማዕከሉ ለ3 ሺህ 989 የቅድመ ከፍያና 3 ሺህ 600 የድህረ ክፍያ ተጠቃሚ ደንበኞች እንዳሉት የገለፁት ስራ አስኪያጁ፤ ገላን ገተማ የትላልቅ ኢንዱስትሪዎች መገኛ መሆኗን ተከትሎ 350 አክቲቭ ሪ አክቲቭ/ ቆጣሪ ተጠቃሚ ደንበኞች አሉት ብለዋል፡፡
 
በከተማዋ ዙሪያ እስከ 28 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚገኙ ዘጠኝ ሳተላይቶች እንዳሉ የገላፁት ስራ አስኪያጁ ከገጠር ደንበኞች በስተቀር ሁሉም የድህረ ክፍያ ተጠቃሚ ደንበኞች ወርሃዊ ፍጆታ ሂሳባቸውን ሙሉ በሙሉ በባንክ በተመቻቹ ዘመናዊና ጊዜ ቆጣቢ የክፍያ አማራጮች እየከፈሉ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ማዕከሉ የኃይል መቆራጥንና መዋዠቅን ለመቀነስ የቅድመ ጥገና ስራዎች እየተሰራ መሆኑን የገለፁት አቶ አለምዘውድ ከኃይል መቆራረጥ ጋር ተያይዞ ከኢንደስትሪ ደንበኞች አልፎ አልፎ ለሚነሱ ቅሬታዎች በልዩ ሁኔታ ቅድሚያ በመስጠት አፋጣኝ ምላሽ እየተሰጠ ነው ብለዋል፡፡
 
በደላላ ከመታልና ከመልካም አስተዳደር ጋር የተያያዙ ቅሬታዎች ይቀርቡ እንደነበር የገለፁት ስራ አስኪያጁ፤ በማዕከሉ በኩል ይህንን ችግር ለመቅረፍ ማንኛውም ደንበኛ አገልግሎት ሲፈልግ ጉዳዩን ህጋዊ ውክልና ካለው ሰው ውጪ ባለጉዳዩ እራሱ እንዲያጨርስ በመደረጉ አንጻራዊ ለውጥ መምጣቱን ተናግረዋል፡፡ሆኖም አንዳንድ ደንበኞችን ህገ-ወጦችን ከማመን አልፎ ውክልና በመስጠት ሳቢያ ለሚደርስ መጭበርበር ተቋሙን ተወቃሽ ሲያደርጉ ይስተዋላል ብለዋል፡፡
 
ብልሹ አሰራሮችን ለመከላከል፤ ለሰራተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ከመስጠት እንዲሁም የደንበኞችን ቅሬታና አቤቱታ ተቀብሎ እርምት ከመውሰድ በተጨማሪ ድርጊቱን ቀድሞ ለመከላከል በዲስትክት ሃላፊዎች ስውር ክትትል የማድረግ ልምድ እንዳለ አንስተዋል፡፡በማዕከሉ ሰራተኞች በኩል ሙያን በማክበር በራስ ተነሳሽነት የመስራት መንፈስ እንዳለ የገለፁት ስራ አስኪያጁ ይህም በዘጠኝ ወር ግምገማው ምርጥ ተሞክሮ ሆኖ ታይቷል ብለዋል፡፡
 
ወቅታዊና ትኩስ የተቋማችን መረጃዎች ወዲያውኑ እንዲደርሳችሁ እነዚህን የትስስር ገፆቻችንን ይወዳጁ፡-
ቴሌግራም፡ t.me/eeuethiopia

Print   Email