የህፃናት ማቆያ ማዕከል ግንባታ አጠናቆ አስመረቀ
የአዲስ አበባ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሰራተኞች የህፃናት ማቆያ ማዕከል ግንባታ አጠናቆ አስመረቀ
የተቋሙ ከፍተኛ ሥራ አመራር በሩብ ዓመት የስራ አፈፃፀም ላይ ውይይት አካሄደ
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከፍተኛ ሥራ አመራር በ2014 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ከጥቅምት 11 – 12 ቀን 2014 ዓ.ም ውይይት አካሂዷል፡፡
አዲስ የገቡት የቆጣሪ መመርመሪያዎች ውጤታማ ሥራ እየሠሩ ነው ተባለ
አዲስ የገቡት የቆጣሪ መመርመሪያዎች ውጤታማ ሥራ እየሠሩ ነው ተባለ
ደንበኞች የተጠቀሙበትን ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳብ በወቅቱ ሊከፍሉ እንደሚገባ ተገለፀ
የድህረ-ክፍያ የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ደንበኞች የተጠቀሙበትን ወርሃዊ ፍጆታ ሂሳብ በወቅቱ ሊከፍሉ እንደሚገባ የዲስትሪቡሽን ሲስተም ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ብዙወርቅ ደምሴ ገልፀዋል፡፡

ለኢንዱስትሪዎች አስተማማኛ የኤሌክትሪክ ኃይል እየቀረበ መሆኑን ተገለፀ

በድሬዳዋ ከተማ የመካከለኛ መስመር የመልሶ ግንባታ ስራ በመከናወኑ በአስተዳደሩ የሚገኙ ከፍተኛ ኃይል ተጠቃሚ ኢንዱስትሪዎች አስተማማኝ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት እያገኙ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ኤሌክትሪክ አገልግሎት የዲስትሪቢዩሽን ሲስተም ቴክኒካል ሰፖርት ኃላፊ አቶ ግርማ ወ/ገብርኤል ገልፀዋል፡፡

00diredawa

ኃፊው እንዳሉት ከዚህ በፊት በእንጨት የተሰሩ የኃይል ማስተላለፊያ ምሰሶዎች በንፋስ ምክንያት በመውደቃቸው ኢንዱስትሪዎቹ ለተደጋጋሚ የኃይል መቆራረጥ በመዳረጋቸው ስራቸውን በአግባቡ እንዳያከናውኑ እንቅፋት ሆኖ መቆየቱን አስታውሰው፤ በተሰራው የመልሶ ግንበታ ስራ ምርታቸውን በሙሉ አቅማቸው እንዲያመርቱ አስችሏቸዋል ብለዋል፡፡

እንደ አቶ ግርማ ገለጻ 38 ኪ.ሜ የመካከለኛ መስመር ዝርጋታ በማከናወን ነባሩን የእንጨት ምሰሶ ሙሉ በሙሉ ወደ ኮንክሪት ምሰሶ መቀየር መቻሉን ጠቁመዋል ፡፡የኮንክሪት ምሰሶ የመቀየር ስራው ለኢንዱስትሪ ፓርክ፣ ለከተማው ውሃና ፍሳሽ፣ ለመኪና መገጣጠሚያ፣ ለስሚንቶ እና ለብረታ ብረት ፍብሪካዎች መሆኑን የጠቀሱት ኃላፊው 760 የኮንክሪት ምሰሶ በመትከል ይስተዋል የነበረውን የኃይል መቆራረጥ መቅረፍ ተችሏል ብለዋል፡፡
00diredawa1
 
አገልግሎቱ የማህበረሰቡን የኃይል ፍላጎት በአስተማማኝ ሁኔታ ተደራሽና ጥራቱን የጠበቀ ለማድረግ ባከናወናቸው እና በሚከናውናቸው ተግባራት አውንታዊ ለውጦች መምጣታቸውን የገለጹት ደግሞ የአገልግሎቱ ስራ አስፈጻሚ አቶ ፍቅረማሪያም አለማየሁ ናቸው፡፡አቶ ፍቅረማሪያም አክለውም አዲስ የኃይል ፍላጊ ደንበኞችንም በተመዘገቡት ቅደም ተከተል መሰረት የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ በስፋት መሰራቱን ጠቅሰዋል፡፡
 
አገልግሎቱ ከዚህ በፊት በመጀመሪያው ምዕራፍ ለኢትዮ ጅቡት የውሃ ፕሮጀክት 37 ኪ.ሜ የመካከለኛ መስመር ዝርጋታ ተከናውኖ 8 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ማቅረብ መቻሉን አስታውሰዋል፡፡
 
በቀጣይም ለኢትዮ ለጅቡቲ ድንበር ተሸጋሪ የውሃ ፕሮጀክት የሚውል ሁለተኛ ምዕራፍ የመካከለኛ መስመር ዝርጋታ ለማከናወን የሚያስችል ፕሮጀክት ለመጀመር የዝግጅት ምዕራፍ ላይ እንደሚገኙ የገለጹት አቶ ፍቅረማሪያም ለግንባታው 46 ኪሎ ሜትር የመካከለኛ መስመር ዝርጋታና 28 ትራንስፎርመሮች እንደሚተከሉ ተናግረዋል፡፡አሁን ላይ የድሬዳዋ አስተዳደር ኤሌክትሪክ አገልግሎት አምስት የአገልግሎት መስጫ ማዕከላት እና ከ69 ሺህ በላይ ደንበኞችን አሉት፡፡
 
ወቅታዊና ትኩስ የተቋማችን መረጃዎች ወዲያውኑ እንዲደርሳችሁ እነዚህን የትስስር ገፆቻችንን ይወዳጁ፡-
ቴሌግራም፡ t.me/eeuethiopia

Print   Email