የኢትዮጽያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በህግ ማስከበርና በህልውና ዘመቻው ካደረገው ሁሉን አቀፋ አስተዋጽኦ ባለፈ በወራሪ ቡድኑ የወደሙ እና የተዘረፋ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶችን በከፋተኛ ርብርብ ጠግኖ እና ገንብቶ ወደ አገልግሎቱ መመለሱ ይታወሳል።
የአማራ ክልል ‘‘በህግ ማስከበርና በህልውና ዘመቻው የተከፈለ መስዋዕትነት ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና አንድነት’’ በሚል መሪ ቃል በባህር ዳር ከተማ ባካሄደው የእውቅና እና የምስጋና መርሀ ግብር ላይ ነው የኢትዮጽያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት እውቅናው የተሰጠው።
በመረሐግብሩ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮችና ከፍተኛ የመንግስት ሃላፊዎች በተገኙበት ተቋሙ ከክቡር ጠቅላይ ሚንስትሩ እጅ የምስጋና እና እውቅና ዋንጫ ተቀብሏል።በሂደቱ ቀን ከሌት የለፋችሁ፣ ከጎናችን በመሆን ድጋፋ ላደረገችሁ፣ ላበረታታችሁን በሙሉ በዚህ አጋጣሚ እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እንወዳለን።
ወቅታዊና ትኩስ የተቋማችን መረጃዎች ወዲያውኑ እንዲደርሳችሁ እነዚህን የትስስር ገፆቻችንን ይወዳጁ፡-
ቴሌግራም፡ t.me/eeuethiopia