የህፃናት ማቆያ ማዕከል ግንባታ አጠናቆ አስመረቀ
የአዲስ አበባ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሰራተኞች የህፃናት ማቆያ ማዕከል ግንባታ አጠናቆ አስመረቀ
የተቋሙ ከፍተኛ ሥራ አመራር በሩብ ዓመት የስራ አፈፃፀም ላይ ውይይት አካሄደ
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከፍተኛ ሥራ አመራር በ2014 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ከጥቅምት 11 – 12 ቀን 2014 ዓ.ም ውይይት አካሂዷል፡፡
አዲስ የገቡት የቆጣሪ መመርመሪያዎች ውጤታማ ሥራ እየሠሩ ነው ተባለ
አዲስ የገቡት የቆጣሪ መመርመሪያዎች ውጤታማ ሥራ እየሠሩ ነው ተባለ
ደንበኞች የተጠቀሙበትን ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳብ በወቅቱ ሊከፍሉ እንደሚገባ ተገለፀ
የድህረ-ክፍያ የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ደንበኞች የተጠቀሙበትን ወርሃዊ ፍጆታ ሂሳብ በወቅቱ ሊከፍሉ እንደሚገባ የዲስትሪቡሽን ሲስተም ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ብዙወርቅ ደምሴ ገልፀዋል፡፡

የሃይል ስርቆትን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት የደንበኞች ሚና ምን ሊሆን ይገባል?

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የአገልግሎት አሰጣጡን ቀልጣፋና ጥራት ያለው ለማድረግ በዘመናዊ ቴክኖሎጅ የተደገፈ አገልግሎት ከመስጠቱም ጎን ለጎን ተከታታይነት ያለው የቆጣሪ ምርመራ ስራዎችን በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡

6666kotar

ተቋሙ በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች በሚገኙ የኤሌክትሪክ ሃይል ተጠቃሚ ደንበኞች ላይ በአደረገው የቆጣሪ ምርመራ ስራ በርካታ የቅድመና የድህረ ክፍያ ቆጣሪዎች ላይ የኤሌክትሪክ ሃይል ስርቆት እየተፈፀመ መሆኑን መገንዘብ ችሏል፡፡

ተቋሙ በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች በሚገኙ የኤሌክትሪክ ሃይል ተጠቃሚ ደንበኞች ላይ በአደረገው የቆጣሪ ምርመራ ስራ በርካታ የቅድመና የድህረ ክፍያ ቆጣሪዎች ላይ የኤሌክትሪክ ሃይል ስርቆት እየተፈፀመ መሆኑን መገንዘብ ችሏል፡፡
 
የኤሌክትሪክ ሃይል ስርቆት የፈፀመ፣ በሕገ-ወጥ መንገድ ከሌላ ጋር ያገናኘ፣ መስመር ያሰናከለ ወይም የኤሌክትሪክ ኃይል ኢንዲሰረቅ ከሌላ መስመር ጋር እንዲገናኝ ወይም መስመሩ እንዲሰናከል ያደረገ ወይም መስመሩ የተሰረቀ፣ በሕገ-ወጥ መንገድ ከሌላ መስመር ጋር የተገናኘ ወይም የተሰናከለ መሆኑ እያወቀ ከዚሁ መስመር የኤሌክትሪክ ኃይል ለፍጆታ ያዋለ ወይም የተገለገለ በኢነርጂ አዋጅ ቁጥር 810/2006 አንቀፅ 28 መሰረት እስከ 5 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት እና እስከ 50 ሺህ ብር በሚደርስ የገንዘብ መቀጮ ይቀጣል፡፡
 
አዋጁን ተላልፎ የሃይል ስርቆት ሲፈፅም የተገኘ ማንኛውም አካል በሕግ ከመጠየቁም በተጨማሪ ይጠቀምበት የነበረው አገልግሎት እንደሚቋረጥ እና ያላግባብ ለተጠቀመው የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳብ በታሪፉ መሰረት ተሰልቶ ከዳግም ማስቀጠያ ክፍያ እና ከቅጣት ገንዘብ ጋር እንዲከፈል ይደረጋል ብለዋል፡፡
ከተቋሙ ጋር ውል ፈፅሞ የኤሌክትሪክ ፍጆታ እንዲጠቀም የተፈቀደለት ማንኛውም ደንበኛ በቤቱ የተገጠመውን ቆጣሪ በመነካካት ወይም ከተፈቀደለት የሃይል አጠቃቀም ውጪ ሲጠቀሙ የተገኙ ደንበኞች አገልግሎቱ የሚቋረጥባቸው ከመሆኑ ባሻገር በፍትሐብሔር እና በወንጀል ህግ ተጠያቂነት የሚያስከትል መሆኑ ተረድቶ በአግባቡ ሊጠቀም ይገባል፡፡
ተቋሙ እየተፈፀመ ያለውን የሃይል ስርቆት ለመከላከልም ሆነ ወንጀሉን የሚፈፅሙ ግለሰቦችን ተጠያቂ ለማድረግ በረካታ ስራዎችን እየሰራ ቢሆንም ደንበኞች ተገቢ የሆነ የቆጣሪ ክትትልና ቁጥጥር በማድረግ ሊከሰት የሚችለውን የወንጀል ተጠያቂነት ሊከላከሉ ይገባል፡፡
 
ይህን ባለማድረግ የሚመጣ ቀድሞ የነበረ የፍጆታ ሂሳብ ዕዳም ሆነ ስርቆት እንዲሁም የወንጀል ጥያቄ የቆጣሪ ባለቤቱ እንደሚሆን ተቋሙ እያሳወቀ ሁሉም የተቋሙ ደንበኞች አስፈላጊ የሆነ ክትትልና ቁጥጥር እንዲሁም ጥንቃቄ ማድረግ የሚያስፈልግ ሲሆን መሰል ህገ-ወጥ ተግባር ሲፈፀም የሚመለከት ደንበኛ በአካባቢው ወደሚገኝ የአገልግሎት መስጫ ማዕከል በአካል በመቅረብ ወይም በ905 ነፃ የጥሪ መስመር በመደወል ማሳወቅ ይገበዋል፡፡
 
ወቅታዊና ትኩስ የተቋማችን መረጃዎች ወዲያውኑ እንዲደርሳችሁ እነዚህን የትስስር ገፆቻችንን ይወዳጁ፡-
ቴሌግራም፡ t.me/eeuethiopia

Print   Email