የህፃናት ማቆያ ማዕከል ግንባታ አጠናቆ አስመረቀ
የአዲስ አበባ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሰራተኞች የህፃናት ማቆያ ማዕከል ግንባታ አጠናቆ አስመረቀ
የተቋሙ ከፍተኛ ሥራ አመራር በሩብ ዓመት የስራ አፈፃፀም ላይ ውይይት አካሄደ
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከፍተኛ ሥራ አመራር በ2014 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ከጥቅምት 11 – 12 ቀን 2014 ዓ.ም ውይይት አካሂዷል፡፡
አዲስ የገቡት የቆጣሪ መመርመሪያዎች ውጤታማ ሥራ እየሠሩ ነው ተባለ
አዲስ የገቡት የቆጣሪ መመርመሪያዎች ውጤታማ ሥራ እየሠሩ ነው ተባለ
ደንበኞች የተጠቀሙበትን ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳብ በወቅቱ ሊከፍሉ እንደሚገባ ተገለፀ
የድህረ-ክፍያ የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ደንበኞች የተጠቀሙበትን ወርሃዊ ፍጆታ ሂሳብ በወቅቱ ሊከፍሉ እንደሚገባ የዲስትሪቡሽን ሲስተም ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ብዙወርቅ ደምሴ ገልፀዋል፡፡

በአገልገሎት አሰጣጡ ላይ የሚታዩ የመልካም አስተዳደር ችግሮች መፍታት እንደሚያስፈልግ ተገለፀ

ይህ የተገለፀው ዛሬ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የዋናው መስሪያ ቤት ሠራተኞች በተቋሙ አጠቃላይ አገልግሎት አሠጣጥ ላይ በሚታዩ የመልካም አስተዳደር ችግሮችና ብልሹ አሰራሮች መፍታት በሚቻልበት ዙሪያ በተወያዩበት ወቅት ነው፡፡

mexico neber

በውይይት መድረኩ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሽፈራው ተሊላ፣ የመሰረታዊ ሰራተኛ ማህበር ሊቀ መንበር አቶ ሃይሉ ዘውዴ፣ የተቋሙ ከፍተኛ ማኔጅመንት አባላትና በኮርፖሬት ደረጃ የሚገኙ የስራ መሪዎችና ሰራተኞች ተሳትፈዋል፡፡

የውይይት መድረኩ ዋና አላማ በተቋሙ አጠቃላይ አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ የሚስተዋሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመለየት የጋራ መግባባት ለመፍጠር እና የመፍትሄ አቅጣጫ ለመስቀመጥ መሆኑንም በዚህ ወቅት ተጠቁሟል፡፡የገቢ ስብሰባ፣ የስነ-ምግባር ችግር፣ የሰው ሃይል ቅጥር፣ የሃብት አጠቃቀምና ንብረት ማስወገድ፣የሰራተኛ ጥቅማጥቅም፣ የግብዓት አቅርቦት፣ የተሸከርካሪና የቢሮ ኪራይ፣ የፕሮጀክት መጓተት፣ የቴክኖሎጂ ትግበራ፣ የውስጥ አሰራር፣ የአስቸኳይ ጥገና፣ 905 የጥሪ ማዕከል አገልግሎት፣ የግዥ ስርዓት መጓተት፣ የስራ ላይ ደህንነት እንዲሁም በሌሎች አገልገሎቶች ላይ የሚስተዋሉ ችግሮች በውይይት መድረኩ የተነሱ ዋና ዋና የመልካም አስተዳደርና የአገልግልት አሰጣጥ ችግሮች መሆናቸውም ተመላክቷል፡፡
mexico nber
የመድረኩ ተሳታፊዎች በተቋሙ ውስጥ በስፋት ይስተዋላሉ ያሉዋቸውን የመልካም አስተዳደር ችግሮችንና የብልሹ አሰራር መንስኤዎችን አንስተው ውይይት አካሂደዋል፡፡
ችግሮቹን ለመከላከልና የደንበኞችን የእርካታ ደረጃ ለማሳደግ ግልፅ የሆነ የቅሬታ ማስተናገጃ ስርዓት መዘርጋት፣ የተጠያቂነት ስርዓት መዘርጋት፣ የተቋሙን የአገልግሎት ስታንዳርድ ማስጠበቅ፣ የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራትን ማሻሻል እና ተከታታይነት ያለው የክትትልና ቁጥጥር ስራ ሊሰራ ይገባል ብለዋል፡፡ተሳታፊዎቹ አክለውም የውስጥ መልካም አስተዳደር ችግሮች ለውጪ የመልካም አስተዳደር ችግር መንስኤ ሊሆኑ ስለሚችሉ ተከታታይነት ያለው የሰራተኛ ውይይት እና የአቅም ማጎልበቻ ስልጠናዎች ሊሰጡ ይገባል ብለዋል፡፡
 
የውይይት መድረኩ የማጠቃለያ ምላሽ የሰጡት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሽፈራው ተሊላ በበኩላቸው የተቋሙ ህልውና የተመሰረተው ከደንበኞች በሚሰበሰብ ገቢ መሆኑን በመገንዘብ የደንበኞቻችንን ቁጥር ማሳደግ እና ለደንበኞቻችን ልዩ ትኩረት መስጠት ይገባናል ብለዋል፡፡
አቶ ሽፈራው አክለውም የመልካም አስተዳደር ችግሮች የተቋሙን ህልውና የሚፈታተኑ በመሆኑ በየደረጃው የሚገኝ የስራ ሃላፊና ሰራተኛ ጥራት ያለውና አስተማማኝ አገልግሎት ሊሰጥ ይገባዋል ሲሉ አሳስበዋል፡፡
የለውጥና መልካም አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክቶሬት አቶ እሱባለው ጤናው በበኩላቸው አብዛኛዎቹ የመልካም አሰተዳደርና የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮች የሚመነጩት ከክትትልና ቁጥጥር ማነስ በመሆኑ ሁሉም የበኩሉን አስተዋፆ ሊያበረክት ይገባል ብለዋል፡፡ከታሳተፊዎች የተነሱ ዋና ዋና ጉዳዮችም በቀጣይ ሁሉት ወራት ለመፍታት ከዋናው መስሪያ ቤት እስከታኛው አደረጃጀት ድረስ ያለው ሠራተኛ ጠንክሮ መስራትና ተገቢውን አገልግሎት መስጠት እንደሚገባው ዳይሬክተሩ ጨምረው ገልፀዋል፡፡
 
ተሳታፊዎችም በተቋሙ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚታዩ የመልካም አስተዳደር ችግሮችና ብልሹ አሰራሮችን ከስርመሰረቱ ለማጥፋት ቁርጠኝነታቸው በማሳየት፤ በቀጣይም ሃላፊነታቸውን በአግባቡ መወጣት እንደሚወጡ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡በመልካም አስተዳደር ላይ የተደረገው ይህ ውይይት በሁሉም የተቋሙ ሪጅኖች፣ ዲስትሪክቶችና አገልግሎት መስጫ ማዕከላት እየተከናወነ ይገኛል፡፡
ወቅታዊና ትኩስ የተቋማችን መረጃዎች ወዲያውኑ እንዲደርሳችሁ እነዚህን የትስስር ገፆቻችንን ይወዳጁ፡-
ቴሌግራም፡ t.me/eeuethiopia

Print   Email