የህፃናት ማቆያ ማዕከል ግንባታ አጠናቆ አስመረቀ
የአዲስ አበባ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሰራተኞች የህፃናት ማቆያ ማዕከል ግንባታ አጠናቆ አስመረቀ
የተቋሙ ከፍተኛ ሥራ አመራር በሩብ ዓመት የስራ አፈፃፀም ላይ ውይይት አካሄደ
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከፍተኛ ሥራ አመራር በ2014 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ከጥቅምት 11 – 12 ቀን 2014 ዓ.ም ውይይት አካሂዷል፡፡
አዲስ የገቡት የቆጣሪ መመርመሪያዎች ውጤታማ ሥራ እየሠሩ ነው ተባለ
አዲስ የገቡት የቆጣሪ መመርመሪያዎች ውጤታማ ሥራ እየሠሩ ነው ተባለ
ደንበኞች የተጠቀሙበትን ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳብ በወቅቱ ሊከፍሉ እንደሚገባ ተገለፀ
የድህረ-ክፍያ የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ደንበኞች የተጠቀሙበትን ወርሃዊ ፍጆታ ሂሳብ በወቅቱ ሊከፍሉ እንደሚገባ የዲስትሪቡሽን ሲስተም ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ብዙወርቅ ደምሴ ገልፀዋል፡፡

ግልፅነትና ተጠያቂነትን ለማስፈን ተከልሶ ወደ ስራ የገባው የተገልጋይ ቻርተር

ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ የሚነሱ ቅሬታዎችን ለመፍታትና የሚስተዋሉ የግልፅነትና ተጠያቂነት ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር ተያይዞ የሚነሱ ችግሮችን ለመቅረፍ የሚያስችል የተገልጋይ ቻርተር በመከለስ ወደ ስራ ማስገባቱ ይታወቃል፡፡

00000eeeeu

ቻርተሩ የተገልጋዮችን መረጃ የማግኘት መብት፣የተገልጋዮችን የባለቤትነት፣ ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት በማረጋገጥ የዜጎችን እርካታ ደረጃ የሚያሳድግ ሲሆን ተቋሙ የሚሰጠውን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ከተገልጋዮች ፍላጎት ጋር የተጣጣመ፣ቀጣይነት ያለውና የተሻሻለ አገልግሎት ሆኖ እንዲቀጥል ለማድረግ ትልቅ ፋይዳ አለው፡፡

የተገልጋይ ቻርተሩ የተቋሙንና የተገልጋዮችን መብቶችና ግዴታዎች በግልጽ እንዲይዝ ተደርጎ የተዘጋጀ በመሆኑ በአገልግሎት አሰጣጥ ሂደቱ ከግንዛቤ ክፍተት ሊፈጠሩ የሚችሉ ቅሬታዎችን በከፍተኛ ሁኔታ ይቀርፋል፡፡
 
ቻርተሩ ደንበኞች ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት የማግኘት መብት እንዳላቸው፣ከጠየቁት አገልግሎት ጋር በተያያዘ መረጃ የማግኘት መብት እንዲሁም በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ቅሬታ የማቅረብ እና መሻሻል የሚገባቸውን ተግባራት ጥቆማ የማድረግ፣ የመፍትሄ ሀሳብ የመስጠት መብት እንዳላቸው በዝርዝር ያስቀምጣል፡፡
 
በአንፃሩ ደግሞ አገልግሎት ለማግኘት የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎችን ማወቅና አሟልቶ መገኘት፣የአገልግሎትና የፍጆታ ሂሳብ በወቅቱ መክፈል፣ ኤሌክትሪክን በውሉ መሰረት ለተፈቀደው ዓላማ ብቻ መጠቀም፣በተቋሙና በደንበኛው የተፈረመውን የውል ስምምነት ማክበር፣ማንኛውም በተቋሙ የተከለከሉ ህገ ወጥ ተግባራትን አለመፈፀም እንዲሁም ተቋሙ እንዲገለገልበት የሰጠውን የኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማቶችን እንደራሱ ንብረት አድርጎ መጠበቅ በቻርተሩ የተቀመጡ የደንበኞች ግዴታዎች ናቸው፡፡
 
በቻርተሩ የተቋሙ መብትና ግዴታዎችም በዝርዝር የተቀመጡ ሲሆን ከነዚህም መካከል የኤሌክትሪክ ቆጣሪን የመመርመር፣ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ክፍያ ሳይከፈል ሲቀር መቁረጥ፣ለጥገና ኤሌክትሪክ መስመር ማቋረጥ ሲኖርበት በቅድሚያ ለደንበኞች በማሳወቅ የማቋረጥ፣ተቋሙ ያፀደቃቸው መመሪያዎችና ደንቦች ሲጣሱ ህግ የጣሰውን ተገልጋይ የገንዘብ መቀጫ ማስከፈልና በህግ መጠየቅ በቻርተሩ የተቀመጡ የተቋሙ መብቶች ናቸው፡፡
 
ከዚህ በተጨማሪ በተገልጋዮች ይዞታ ውስጥ የቆጣሪ አቀማመጥን የመወሰን፣ በተቋሙ የተሰጡ የስራ ስታንዳርዶችን ለማያሟሉ ኃይል ፈላጊዎች የኃይል አቅርቦት የመከልከል፣በኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማትና ቁሳቁሶች ላይ ለሚደርሱ ጉዳቶች የጉዳት ካሳ የመጠየቅ መብት እንዳለውም በቻርተሩ ተቀምጧል፡፡
 
በሌላ በኩል ደህንነቱና ጥራቱ የተጠበቀ የኤሌክትሪክ አገልግሎት የመስጠት፣ለደንበኞች በገባው ውል መሰረት በቂ የኤሌክትሪክ አገልግሎት የማቅረብ፣በጥገናና በልዩ ልዩ ምክንያት የሚቋረጥን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ለተገልጋዩ ቀድሞ የማሳወቅና ቅድመ ጥንቃቄ እንዲደረግ የመግለፅ ግዴታ እንዳለበት ቻርተሩ ያስገነዝባል፡፡
ለአገልግሎት አሰጣጥ የወጡ ስታንዳርዶችን አክብሮ የመስራት እንዲሁም ተገልጋዮች ኤሌክትሪክ ሲቋረጥባቸው እና መረጃው ለተቋሙ ሲደርስ በዚህ ቻርተር ላይ የተጠቀሙትን ስታንዳርዶች ጠብቆ አገልግሎቱን መልሰው እንዲያገኙ የማድረግ የተቋሙ ግዴታዎች እንደሆኑ በዝርዝር ተቀምጧል፡፡
በተጨማሪም በዋናው መ/ቤት፣በክልል ኤሌክትሪክ አገልግልት ጽ/ቤቶች፣በዲስትሪክት ኤሌክትሪክ አገልግሎት ቢሮዎች እና በአገልግሎት መስጫ ማዕከላት የሚሰጡ አገልግሎቶች በቻርተሩ በዝርዝር ተቀምጠዋል፡፡
 
ደንበኞች አገልግሎት ፈልገው ሲመጡ ማሟላት ስለሚገባቸው ቅድመ ሁኔታዎች፣በ905 ነጻ የጥሪ ማዕከል የሚሰጡ አገልግሎቶች፣ የፍጆታ ሂሳብ መክፈያ ዘዴዎችና አማራጮች፣ የጉዳት ካሳ አከፋፈል፣ ኃይል ቁጠባ፣ የኤሌክትሪክ ታሪፍና የአገልግሎት ክፍያ ሂሳብ፣የተገልጋዮች ቅሬታ አቀራረብና አፈታት ደንብ እንዲሁም የተቋሙ ባለድርሻ አካላትና ሚናቸውን በተመለከተ በቻርተሩ እንዲካተት ተደርጎ ተዘጋጅቷል፡፡
ወቅታዊና ትኩስ የተቋማችን መረጃዎች ወዲያውኑ እንዲደርሳችሁ እነዚህን የትስስር ገፆቻችንን ይወዳጁ፡-
ቴሌግራም፡ t.me/eeuethiopia

Print   Email