የህፃናት ማቆያ ማዕከል ግንባታ አጠናቆ አስመረቀ
የአዲስ አበባ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሰራተኞች የህፃናት ማቆያ ማዕከል ግንባታ አጠናቆ አስመረቀ
የተቋሙ ከፍተኛ ሥራ አመራር በሩብ ዓመት የስራ አፈፃፀም ላይ ውይይት አካሄደ
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከፍተኛ ሥራ አመራር በ2014 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ከጥቅምት 11 – 12 ቀን 2014 ዓ.ም ውይይት አካሂዷል፡፡
አዲስ የገቡት የቆጣሪ መመርመሪያዎች ውጤታማ ሥራ እየሠሩ ነው ተባለ
አዲስ የገቡት የቆጣሪ መመርመሪያዎች ውጤታማ ሥራ እየሠሩ ነው ተባለ
ደንበኞች የተጠቀሙበትን ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳብ በወቅቱ ሊከፍሉ እንደሚገባ ተገለፀ
የድህረ-ክፍያ የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ደንበኞች የተጠቀሙበትን ወርሃዊ ፍጆታ ሂሳብ በወቅቱ ሊከፍሉ እንደሚገባ የዲስትሪቡሽን ሲስተም ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ብዙወርቅ ደምሴ ገልፀዋል፡፡

አምራች ኢንዱስትሪዎች የኃይል አቅርቦት ችግር እንዳይገጥማቸው እገዛ እየተደረገ ነው

የአምራች ኢንዱስትሪ ደንበኞች በሙሉ አቅማቸው እንዲያመርቱ በኃይል አቅርቦት በኩል ችግር እንዳይገጥማቸው እገዛ እየተደረገ መሆኑን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የኢንዱስትሪ ደንበኞች የኃይል አቅርቦት ማስተባበሪያ ኃላፊ አቶ ነብዩ በየነ ተናግረዋል፡፡ይህም የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ከመደገፍ አንፃር ሲታይ ድርሻው ትልቅ እንደሆነ ኃላፊው አብራርተዋል፡፡

001industry

ተቋሙ ያልተማከለ አደረጃጀትን ተግባራዊ ባደረገበት ወቅት የኢንዱስትሪ ደንበኞች የኃይል አቅርቦት ማስተባበሪያው ድርሻ ለክልሎች ተትቶ የነበረ ቢሆንም፤ ባለድርሻ አካላት እና ኢንቨስተሮች ከአንድ መስኮት መረጃና አገልግሎት ለማግኘት እንዳይቸገሩ በተቋሙ በኩል ምቹ ሁኔታን ከመፍጠር አንፃር በ2010 ዓ.ም በድጋሚ እንደተቋቋመ ገልፀዋል፡፡

ማስተባበሪያው ከተለያዩ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ጋር በመቀናጀት ተቋሙ የተጣለበትን ሃገራዊ ተልዕኮ እንዲወጣ እየሰራ መሆኑን ጠቅሰው፤ ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን፣ ከኢ.ፌ.ድ.ሪ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን፣ ከኢንዱስትሪ ሚኒስቴር፣ ከግብርና ሚኒስቴር እና ከማዕድን ሚኒስቴር ጋር በጋራ እንደሚሰራም አስታውቀዋል፡፡
ooindustry
በዚህም የውጪ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንቶችን፣ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ የሚገኙ ኢንዱስትሪዎችን፣ ከውጭ ሀገር የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ወስጥ ለመተካት የሚሰሩ አምራች ድርጅቶችን፣ የአበባ ልማቶችን እንዲሁም የብረታ ብረት፣ የኬሚካልና ኮንስትራክሽን ግብዓት አቅራቢ ድርጅቶችን በሙሉ አቅማቸው እንዲያመርቱ ለማገዝ እየተሰራ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡
ከኢንቨስተሮች ወደ ማስተባበሪያ ክፍሉ የሚመጡ የአዲስ ኃይል ጥያቄ፣ የኃይል መቆራረጥ፣ የኃይል ማሻሻያ እና ከቢል ጋር የተያያዙ ጥያቄዎችን ተቀብሎ እንዳስፈላጊነቱም ጥናት በማድረግ ለጥያቄዎቻቸው መፍትሄ እንደሚሰጥ ኃላፊው ተናግረዋል፡፡
እንደ አቶ ነብዩ ገለፃ ለልማት በተለያዩ አካባቢዎች የኃይል ማሰራጫ ጣቢያ አቅም እንዲሻሻል እና አዳዲስ መስመሮች ለባለሀብቶች እንዲዘጋጁ ከማድረግ አንጻር አዲስ መሰረተ ልማቶችን እስከመገንባት ድረስ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ጋር በመቀናጀት አስፈላጊው አገልግሎት ይሰጣል፡፡
በ2014 በጀት ዓመት አዲስ ኃይልና ተጨማሪ ኃይል ለሚፈልጉ ኢንዱስትሪዎች ከባለድርሻ አካላት እና ከክልሎች ጋር በሚደረገው ጥረትና መናበብ ያሉ ክፍተቶችን በመለየት የእቅዱን 87 ነጥብ 7 በመቶ መፍታት መቻሉን ጠቁመዋል፡፡
 
እንዲሁም ባለፉት ዘጠኝ ወራት የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ተደራሽነትን ከማሳደግ አንጻር ለማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎች 114 ኪ.ሜ መስመር ለመዘርጋት ታቅዶ፤ 145 ኪ.ሜ በመዘርጋት 59 ኢንዱስትሪዎች የአዲስ ኃይል እና ተጨማሪ ኃይል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ መቻሉን ጠቁመው፤ ለ41 የአበባ አምራቾች ፍላጎት ደግሞ ተገቢው ምላሽ መሰጠቱን ኃላፊው አስረድተዋል፡፡
 
በውጪ ምንዛሬ እጥረት ምክንያት የግንባታ ግብዓት አቅርቦት እስከ አንድ አመት መዘግየት፣ ባለሀብቱ የሚያቀርባቸው የኤሌክትሪክ እቃዎች በወቅቱ ያለመቅረብ፣ አንዳንድ ባለሀብቶች መክፈል የሚጠበቅባቸውን ክፍያ አለመክፈልና ማዘግየት የታዩ ተግዳሮቶች መሆናቸውም አንስተዋል፡፡
 
በአንዳንድ አካባቢዎች የሚገኙ ሰብስቴሽኖች አቅም መሙላት እንዲሁም ኢንዱስትሪዎቹ የሚያቀርቡት የኃይል ፍላጎትና አጠቃቀም አለመመጣጠን ማለትም የተሰጣቸውን የኃይል መጠን በአግባቡ አለመጠቀም እና የነባር ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎች አመሰራረት በኢንዱስትሪ ዞን የተጠቃለለ አለመሆን በኤሌክትሪክ መሰረት ልማት ግንባታ እና ማሻሻያ ላይ ተግዳሮት እንደሆኑባቸው ኃላፊው አክለው አንስተዋል፡፡
 
በተጨማሪም በተወሰኑ አካባቢዎች የነበረው የፀጥታ ችግር፣ በተለያዩ አካባቢዎች የሰራተኞች የደህንነት ስጋት፣ የግንባታ ግብዓት ስርቆት እንዲሁም ከሲሚንቶ እና ብረት ዋጋ መናር ጋር ተያይዞ የምሰሶ አቅርቦት ማነስ በስራ ሂደቱ የሚያጋጥሙ መሰናክሎች መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡በመጨረሻም የተጠቀሱት ተግዳሮቶች ያሉ ቢሆንም በተቻለ መጠን ችግሮችን ለመፍታት ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት በመስራት ደንበኞቻቸውን ለማርካት እየሰሩ መሆናቸውን አቶ ነብዩ ተናግረዋል፡፡
ወቅታዊና ትኩስ የተቋማችን መረጃዎች ወዲያውኑ እንዲደርሳችሁ እነዚህን የትስስር ገፆቻችንን ይወዳጁ፡-

Print   Email