የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከፍተኛ ሥራ አመራር የ2014 በጀት ዓመት ያለፈውን ዘጠኝ ወር የሥራ አፈፃፀም ግምገማ ዛሬ በቢሾፍቱ ከተማ ማካሄድ ጀምሯል፡፡
ግምገማውን የተቋሙ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሽፈራው ተሊላ የመክፈቻ ንግግር በማድረግ አስጀምረውታል፡፡ ለሶስት ቀናት በሚቆየው በዚህ ግምገማ፤ ያለፈው ዘጠኝ ወር በተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራቶች ላይ ውይይት ይካሄዳል፡፡
በዚህ ግምገማ ላይ የዘጠኙ ክልሎችና የሁለቱ የከተማ አስተዳደር ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጽ/ቤት ስራ አስፈጻሚዎች እንዲሁም በየደረጃው ያሉ ዳይሬክተሮች አፈጻጸማቸውን ከእቅዳቸውን ጋር በማነፃፀር ያቀርባሉ፡፡

ወቅታዊና ትኩስ የተቋማችን መረጃዎች ወዲያውኑ እንዲደርሳችሁ እነዚህን የትስስር ገፆቻችንን ይወዳጁ፡-
ቴሌግራም፡ t.me/eeuethiopia