የህፃናት ማቆያ ማዕከል ግንባታ አጠናቆ አስመረቀ
የአዲስ አበባ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሰራተኞች የህፃናት ማቆያ ማዕከል ግንባታ አጠናቆ አስመረቀ
የተቋሙ ከፍተኛ ሥራ አመራር በሩብ ዓመት የስራ አፈፃፀም ላይ ውይይት አካሄደ
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከፍተኛ ሥራ አመራር በ2014 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ከጥቅምት 11 – 12 ቀን 2014 ዓ.ም ውይይት አካሂዷል፡፡
አዲስ የገቡት የቆጣሪ መመርመሪያዎች ውጤታማ ሥራ እየሠሩ ነው ተባለ
አዲስ የገቡት የቆጣሪ መመርመሪያዎች ውጤታማ ሥራ እየሠሩ ነው ተባለ
ደንበኞች የተጠቀሙበትን ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳብ በወቅቱ ሊከፍሉ እንደሚገባ ተገለፀ
የድህረ-ክፍያ የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ደንበኞች የተጠቀሙበትን ወርሃዊ ፍጆታ ሂሳብ በወቅቱ ሊከፍሉ እንደሚገባ የዲስትሪቡሽን ሲስተም ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ብዙወርቅ ደምሴ ገልፀዋል፡፡

19 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር ከበጎ ፍቃድ ሥራ መሰብሰብ መቻሉ ተገለፀ

የድሬዳዋ ሪጅን ኤሌክትሪክ አገልግሎት በስምንት ተከታታይ ቅዳሜ ቀን በሰጠው የበጎ ፍቃድ አገልግሎት 19 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር ማሰባሰቡን አስታወቀ፡፡

000dire11

አገልግሎቱ ብሩን ማሰበባሰብ የቻለው ከ11 ሺህ 160 ደንበኞች መሆኑን በቢሾፍቱ ከተማ እየተከናወነ ባለው የ9 ወር እቅድ አፈፀፀም ላይ ተነግሯል፡፡

የሪጅኑ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሥራ አስፈፀሚ አቶ ፍቅረማሪያም አለማየው በነፃ አገልግሎት ከተቋሙ ሊወጣ የሚችል 2 ሚሊዮን 767 ሺህ 567 ብር ከወጪ ማዳኑን ተናግረዋል፡፡ በበጎ ፍቃድ ሥራ የ767 የቆረጣ ቅጠላ፣ የ360 ቆጣሪ ምርመራ፣ 408 ምች ተከላ መከናወናቸውን ሥራ አስፈፃሚው አስታውቀዋል፡፡
 
000dire3456
በመረጃ ሥራዓቱ ያልተፈቱ 14 ኪ.ሜ የዛፍ ቆረጣ፣ 643 ቅሬታዎች ከተሠሩት ሥራዎች ውስጥ መሆናቸው ከቀረበው የሥራ አፈፀፀም ለማወቅ ተችሏል::በድሬዳዋ በጎ ፍቃድ ሥራው ውዝፍ ሥራዎችን ከማቃለለም ባለፈ የገቢ አሰባሰብ ምጣኔን ከ100 ፐርሰንት በላይ ማሳካት ማስቻሉን በቀረበው መረጃ ተመላክቷል።
 
የበጎ ሥራው ከሁለት ወር በፊት የጀመረ ሲሆን እስከ ሰኔ መጨረሻ እንደሚቆይ አቶ ፍቅረማሪያም ጠቁመዋል፡፡በበጎ ፍቃድ ሥራው ላይ የከታማዋ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሠራተኞች የማኔጅምንት አባላት መሳተፋቸውን ከቀረበው መረጃ መታዘብ ተችሏል፡፡
 
ለበጎ ሥራው መነሻ አገልግሎቱ በጦርነቱና በተለያዩ ግጭቶች የደረሰበት ኪሣራ፣ የተከማቹ ውዝፍ ሥራዎች የፈጠሩት የመለካም አስተዳደር ችግሮች መንስኤ መሆናቸው በምክንያትነት ተጠቅሰዋል፡፡
ወቅታዊና ትኩስ የተቋማችን መረጃዎች ወዲያውኑ እንዲደርሳችሁ እነዚህን የትስስር ገፆቻችንን ይወዳጁ፡-
ቴሌግራም፡ t.me/eeuethiopia

Print   Email