የህፃናት ማቆያ ማዕከል ግንባታ አጠናቆ አስመረቀ
የአዲስ አበባ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሰራተኞች የህፃናት ማቆያ ማዕከል ግንባታ አጠናቆ አስመረቀ
የተቋሙ ከፍተኛ ሥራ አመራር በሩብ ዓመት የስራ አፈፃፀም ላይ ውይይት አካሄደ
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከፍተኛ ሥራ አመራር በ2014 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ከጥቅምት 11 – 12 ቀን 2014 ዓ.ም ውይይት አካሂዷል፡፡
አዲስ የገቡት የቆጣሪ መመርመሪያዎች ውጤታማ ሥራ እየሠሩ ነው ተባለ
አዲስ የገቡት የቆጣሪ መመርመሪያዎች ውጤታማ ሥራ እየሠሩ ነው ተባለ
ደንበኞች የተጠቀሙበትን ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳብ በወቅቱ ሊከፍሉ እንደሚገባ ተገለፀ
የድህረ-ክፍያ የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ደንበኞች የተጠቀሙበትን ወርሃዊ ፍጆታ ሂሳብ በወቅቱ ሊከፍሉ እንደሚገባ የዲስትሪቡሽን ሲስተም ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ብዙወርቅ ደምሴ ገልፀዋል፡፡

በህገ ወጥ መንገድ በተገጠሙ 23 ቆጣሪዎች ላይ እርምጃ ተወሰደ

በፊንፍኔ ዙሪያ ዲስትሪክት በአንፎ አገልግሎት መስጫ ማዕከል ስር ፀበል ማዶና ከወይብላ ማርያም ጀረባ በሚገኙ መኖሪያ ቤቶች በተደረገ የቁጥጥር ስራ በህገ ወጥ መንገድ በተገጠሙ 23 የኤሌክትሪክ ቆጣሪዎች ላይ ትናንት ሚያዝያ 19 ቀን 2014 ዓ.ም እርምጃ መወሰዱን የማዕከሉ ሥራ አስኪያጅ አቶ ሃይሉ በቀለ ገልፀዋል፡፡

000serkot1

ቆጣሪዎች የተገጠሙት በህገወጥ ደረሰኝ ማንነታቸው ለጊዜው ባልታወቁ ግለሰቦች መሆኑን አቶ ሃይሉ አሳውቀዋል፡፡ ሆኖም ከ23 ውስጥ 21 ቆጣሪዎች ተቋሙ ያስመለሳቸው ሲሆን፤ ሁለቱ ግን ተጠቃሚዎቹ አስቀድመው ማሸሻቸውን አመላክተዋል፡፡

ዲስትሪክቱና አገልግሎት መስጫ ማዕከሉ ከአንፎ ፖሊስና ሚሊሻ ጋር በጋራ ባደረጉት ቅንጅት እርምጃው መወሰዱን ገልፀው፤ እስካሁን ከተቋሙ እውቅናና አሰራር ውጭ ለአደጋ አጋላጭ በሆነ መንገድ ጭምር ለረጅም ጊዜ ሲጠቀሙ እንደነበር ሥራ አስኪያጁ ጨምረው ተናግረዋል፡፡
000serkot22
በህገ ወጥ መንገድ የገቡት በእነዚህ ቆጣሪዎች፤ ለጊዜው ማንነታቸው ያልታወቁት ግለሰቦቹ ከእያንዳንዳቸው 20 ሺህ ብር እንደተቀበሉባቸው የፊንፍኔ ዙሪያ ዲስትሪክት የህግ አገልገሎት ሥራ አስኪያጅ አቶ የኃላእሽት አብረሀም ገልፀዋል፡፡
በዚህ ተግባር ላይ የተሰማሩ አካላት ተጠያቂ ለማድረግ ምርመራ መጀመሩና በቀጣይም ተገቢውን ህጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ ሥራ አስኪያጁ ጨምረው ጠቁመዋል፡፡
አዲስ የኤሌክትሪክ ቆጣሪ የሚፈልግ ማንኛውም ግለሰብ ተቋሙ ያስቀመጠውን ተገቢውን ህጋዊ አሰራር ብቻ በመከተል ማግኘት የሚችል መሆኑን አውቆ፤ ከደላሎችና ህገ ወጥ ተግባር ከሚፈፅሙ አጭበርባሪዎች ራሱን እንዲጠብቅ አንዲሁም ለመሰል ወንጀሎች ተባባሪ እንዳይሆን አቶ የኃላእሽት አሳስበዋል፡፡
ወቅታዊና ትኩስ የተቋማችን መረጃዎች ወዲያውኑ እንዲደርሳችሁ እነዚህን የትስስር ገፆቻችንን ይወዳጁ፡-
ቴሌግራም፡ t.me/eeuethiopia

Print   Email