በህገ-ወጥ መንገድ በተዘረጉ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ
በአዲስ አበባ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የምስራቅ አዲስ አበባ ዲስትሪክት ቁጥር 5 አገልግሎት መስጫ ማዕከል በከተማው በህገ-ወጥ መንገድ የተዘረጉ የኤሌክትሪክ መስመሮችን የማፍረስና የተገጠሙ ቆጣሪዎችን የማንሳት እርምጃ ወስዷል፡፡
እርምጃው የተወሰደው ልዩ ስሙ ወጂ መድሐኔአለም ሰፈር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ሲሆን፤ ግለሰቦቹ በህገ-ወጥ መንገድ የኤሌክትሪክ መስመሮች ዘርግተው የኤሌክትሪክ ቆጣሪ ሲጠቀሙ እንደነበር የአዲስ አበባ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የህግ ጉዳዮች ሥራ አስኪያጅ አቶ ታሪኩ ማዕረጉ ገልፀዋል፡፡
ዲስትሪክቱ ጥራት ያለው አገልግሎት ለመስጠት በትኩረት እየሰራ መሆኑን ገለፀ
በአማራ ከልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት የደብረ ብርሃን ዲስትሪክት ጥራት ያለውና አስተማማኝ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ለመስጠት በትኩረት እየሰራ መሆኑን አስታውቋል፡፡
የዲስትሪክቱ ዳይሬክተር አቶ ሙሉጌታ ደሳለኝ እንደገለፁት፡- ዲስትሪክቱ የደንበኞችን ቅሬታዎች ደረጃ በደረጃ ለመፍታት፣ የኃይል መቆራረጥና መዋዥቅን ለመቀነስ፣ የመልሶ ግንባታ ስራዎችን ለማጠናከር እና ከባለፈው በጀት ዓመት የተሻለ ገቢ ለመሰብሰብ ትኩረት ሰጥቶ በመንቀሳቀስ ላይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
አዳዲስ የመካከለኛ ኢንዱስትሪ ኢንተርፕራይዞች ኤሌክትሪክ አገኙ
በአዲስ አበባ ከተማ 102 አዳዲስ የመካከለኛ ኢንዱስትሪ ኢንተርፕራይዞች ኤሌክትሪክ ማግኘታቸው ተጠቁሟል፡፡ በከተማው በስራ ኢንተርፕራይዝ እና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ወደ መካከለኛ ኢንዱስትሪ ኢንተርፕራይዝ አድገው የሁለተኛ እና ሶስተኛ ዙር የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ክፍያ ሙሉ ለሙሉ ያጠናቀቁ ኢንዱስትሪዎች 8 ትራንስፎርመሮች ተተክሎ ኤሌክትሪክ እንዲያገኙ ተደርጓል፡፡
የሲዳማ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጽ/ቤት በይፋ ስራ ሊጀምር ነው
የሲዳማ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጽ/ቤት ከሚቀጥለው ሐምሌ /2014 ዓ.ም ጀምሮ ስራውን በይፋ ሊጀምር እንደሆነ ተገልጿል፡፡ ይህ የተገለፀው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የቦርድ ሰብሳቢ ዶክተር ኢንጅነር ጌታሁን መኩሪያ፣ የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት አቶ ደስታ ሌዳሞ፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሽፈራው ተሊላ፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከፍተኛ የማናጅመንት አባላት እና የደቡብ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ማናጅመንት አባላት በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ቢሮ ግንቦት 12/2014 ዓ.ም ባደረጉት የጋራ ስብሰባ ላይ ነው፡፡
የገንዘብ ቁጠባና ብድር ማህበሩ እና የሠራተኛው ተጠቃሚነት
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ የህብረት ስራ ማህበር በቀድሞ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ስራ አስኪያጅ ኮለኔል ተሰማ አባደራሽ በሃምሌ 1 ቀን 1975 ዓ.ም በ 3 ሺህ 29 አባላት በ205 ሺህ 516 ብር መነሻ ካፒታል ተቋቁሟል፡፡
ሠራተኛው ጠንካራ የኢኮኖሚ መሰረት እንዲኖረው እንዲሁም በወቅቱ የነበረውን የመኖረያ ቤት ግንባታ ችግር ከግምት ውስጥ በማስገባት አባላቱን የቤት ባለቤት ለማድረግ፣ የቁጠባ ባህላቸውንም ለማሳደግ ሲባል የተቋቋመ ማህበር ነው ሲሉ የማህበሩ ሥራ አስኪያጅ አቶ መዝገቡ ታከለ ገልፀዋል፡፡